Sunday, August 11, 2013

የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ገ/እግዚአብሔር ኪደ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፭ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው “ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “አልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ሺህ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡

Thursday, August 8, 2013

ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀና የማያመሰኩ እንስሳት (የዘመናችን ተሐድሶዎች)

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ሠለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ማን ነው ለሚለው የተሐድሶዎች ጥያቄ የቀረበ መልስ

ሰሞኑን በተለይ በርከት ባሉት በመጽሐፈ ገጽ ወዳጆቼ በኩል  ‹‹ ሠለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ማን ነው? ›› የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ቀርቦልኛል፡፡ በተሐድሶዎች በተሰራጨ አንድ የቪዲዮ ቁራጭ ላይ በሦስቱ ድርሳናት ማለትም በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል በድርሳነ ሩፋዔል ላይ ደግሞ ሩፋኤል አዳናቸው ተብሎ ስለተገለጸ ትክክሉ የቱ ነው፤ በርግጥ ያዳናቸውስ ማን ነው የሚል ነው፡፡ በዚያም ጊዜ ሆነ ዛሬ ከአንዳንዶቹ መልእክት እንደተረዳሁት የድንጋጤ ስሜትም የተሰማቸው አሉ፡፡ ይህን ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶችንም ስመለከት ለጉዳዩ ቢያንስ አንዲት ትንሽ መጣጥፍ እንዳአቅሜ  እንኳ ለጊዜው መስጠት እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ጥያቄውን ለላካችሁልኝ ሁሉ ይህችን መቆያ እንካችሁ ብያለሁ፡፡ ዋናው ወይን ሁልጊዜም ወደ ኋላ መምጣቱ አይቀርምና እርሱን አብረን ከወይን አዳዩ እንጠብቃለን፡፡

Tuesday, August 6, 2013

የውዳሴ ማርያም ትርጓሜ- መግቢያ

ገ/እግዚአብሔር ኪደ
                                                                                  
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- ውዳሴ፡- “ወደሰ” ከሚል ግስ የወጣ ሲኾን ትርጓሜውም ማወደስ፣ መወደስ፣ አወዳደስ፣ ውደሳ፣ ምስጋና… ማለት ነው፡፡ “ውዳሴ ማርያም”        ሲልም የማርያም ምስጋና ማለት ነው፡፡
  የውዳሴ ማርያም መጽሐፍ ጸሐፊ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ሲኾን መጽሐፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በጣም የታወቀና የተወደደ የጸሎት መጽሐፍ ነው። ይኸውም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በብዙ ምሳሌ እየመሰለ የሚያወድስ፣ ዘለአለማዊ ድንግልናዋን የሚያስተምር፣  በስነ ጽሑፋዊ ይዘቱም እጅግ ውብ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማመስገን የተጻፈ ይኹን እንጂ በውስጡ እጅግ ረቂቅ የኾነ የስነ መለኮት ትምህርት (ለምሳሌ ስለ ምሥጢረ ሥላሴና ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ ) የያዘ መጽሐፍ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የቆሎ ተማሪዎች በቃል ትምህርቱ ዘርፍ ከየዘወትር ጸሎት ቀጥለው በንባብና በዜማ ይህን ውዳሴ ማርያም የተባለውን የትምህርት ክፍል ይማሩታል።
 ለጊዜው ይኸን እናቈየውና ወደ ተነሣንበት ዓላማ እንመለስ፡፡ በቀጥታ ወደ ትርጓሜው ከመግባታችን በፊትም ስለ ጸሐፊው ዜና መዋዕል በትንሹም ቢኾን በዚህ ክፍል ልናስቃኛችሁ ወድደናልና ተከታተሉን፡፡ መልካም ንባብ!

Monday, August 5, 2013

ፈቃደ እግዚአብሔር፤ ክፍል አራት (የመጨረሻው ክፍል)

በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም.)፡- የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምን አውቃለሁ? የሚለው ጥያቄ በራሱ በእኛ ውስጥ የተለየ ምልክት መሻት መኖሩን ያመለክታል፡፡ ይህን ዐይነት ምልክትን የመሻት አካሔድ ደግሞ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ባለፈው ጊዜ በሦስተኛው ክፍል ጽሑፍ አይተን ነበር፡፡ ለቅዱሳን የሚደረገው መገለጥ ራሱ ቅዱሳን ራሳቸውን ክደው ሙሉ በሙሉ ማንነታቸውን ለእግዚአብሔር ስለሰጡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማለትም መጻኢው ቀድሞ በእነርሱ የሚገለጸው የደረሱበትን መዓርግ ለማሳየት ነው እንጂ በእያንዳንዱ ነገር ላይ ምልክትን እየሻቱ ያም እየተደረገላቸው አይደለም፡፡ ታዲያ እኛ ኃጥአኑና ደካሞቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዴት ልናውቅ እንችላለን? ይህን ጥያቄ ለመረዳት አስቀድመን ስለ ፈቃደ እግዚአብሔር ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን እንመለከታለን፡፡

FeedBurner FeedCount