Sunday, March 2, 2014

ቅድስት ዘሠኑይ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 23 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ ከምቅድመንባበ ዝንቱ ክርታስ

ይኄይሰኒ ሕገ አፉከ እምአእላፍ ወርቅ ወብሩር ወይጥእም እመዐር ወሶከር - ከብዙ ወርቅና ብር የአፍህ ህግ ይሻለኛል፡፡ እንደ ስኳርና እንደ ማር ይጥማልና፡፡በሚጥም አንደበቱ ጌታ አክብሮ አንደበቱን ያጣፈጠለት ዜመኛ የሰኞ ቅድስት ድርሰቱን ሲጀምር ባዜመበት ቃል ጀምረንንጉሰ ሰላም ሰላመከ ሀበነ - የሰላም ንጉሷ ሰላምህን ስጠንብለን እኛም ከእርሱ ጋር በማዜም በተሰጠን ሰላም ከዛሬ የድርሰቱን አንዳንድ ቃላትን እንላለን፡፡

Saturday, March 1, 2014

ቅድስት (ይህች ዕለት የተቀደሰች ናት)


(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 22 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ

ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ
 ከአንድ ግንድ ላይ በቅለን ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ አካል ሆነን ከአንዱ ከኢየሱስ ማዕድ የምንበላ የአንዱ አባት ልጆች የሆንን እንደ ብሉይ ሳይሆን በእርሱ ስም ተሰይመን በእርሱ ክርሰቲያን የምንባል አንድነታችን በሞት እንኳን የማይፈታ ቤተሰቦቼ ! ዘለዓለማዊ በሆነው በእርሱ ሰላምታ ደስታ ይሁንላችሁ እላላሁ ። ይህ የሚገባ ነውና ደስ ያላችሁ ደስ ይበላችሁ ብዬ ሰላምታዬን ወደ እናንተ ላክሁ።

Thursday, February 27, 2014

ዘወረደ ዘቀዳሚት ሰንበት



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ

(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 21 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

 እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላምን አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና፡፡ቆላ 1÷19-20 ይህ የመስቀሉ ደም ለደማውያኑም ለመንፈሣውያንም ፍጥረት ፍጹምና ዘለዓለማዊ ሰላምን ሰጥቷል፡፡ ታዲያ እኔም በማትከፈል ሦስትነት በአንድ ሕልውና በምትሆን በእግዚአብሔር ሰላምታ ዘለዓለማዊው ሰላም ይደረግልን ብዬ የአባቴን የቅዱስ ያሬድን የቀዳሚት ሰንበት ዘወረደ ጾመ ድጓ በጥቂቱ የተመረጡ ቃላት እነሆ፡፡

ዘወረደ ዘዐርብ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
 
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 21 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ
ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ 

 የጽዮን አምሳያ ለሆነችው ቤተክርስቲያን እንዲህ ይላል ቅዱስ አባት ዜመኛው ኢትዮጵያዊጎሕ ጎሐ ወኮነ ጽባሐ ንሳለማ ለጽዮን ምክሐ እምነ በሀ - ሌሊቱ ነጋ ጠዋትም ሆነ መመኪያችን እናታችን ጽዮን እንሳለማት፡፡” እኔም በቤተክርስቲያን ጡቶች ያደግሁ ከእርሷ በሚሆን ወተት ላደጉና ለኖሩ ምዕመናን እናታችን ለምትሆን ለቤተክርስቲያን ዜመኛው በሰጣት ሰላምታ የጽዮን ልጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ ይሁን ሰላማችሁ ይብዛ፡፡ ትናንት በቅኔ ማሕሌት እንደተኛው ከበሮ (ከበሮ አገልግሎት በዚህ ወቅት አይሠጥም) ሳይሆን የድካም የሆነ ወዝ (ላብ) ከማይታይበት ከላይ ታች፣ ከግራ ቀኝ፣ ወደፊት ወደኋላ በሚለው መቋሚያ እየታገዝን ዜማውን በቤተክርስቲያን ስለቤተክርስቲያን ሠምተናል፡፡ ዛሬም እንዲሁ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን (ጽዮን) እና ቅዱስ መስቀል በመሃልም መልካም ቃለ እግዚአብሔር እንሠማለን፣ የአባታችን አምላክ ከመላእክቱ ጋር ያሰልፈን፡፡

FeedBurner FeedCount