Friday, June 15, 2012

ልዩ ፍርድ ቤት- በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ!!


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  “የብዙዎቻችን ከንፈሮች ለሐሜት የተከፈቱ ናቸው፡፡ የራሳችንን ግንድ ትተንም ከሰዎች ጉድፍን ለማውጣት እንዳዳለን፡፡ በወንድሞቻችንም ላይ እንፈርዳለን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! እንጠንቀቅ! የፍርድ ዙፋን ያለው ከእርሱ ጋር ብቻ ነውና የወልድን ሥልጣን እኛው አንያዘው፡፡
መፍረድ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ምንም የማያስወቅስና በጣም ብዙ ጥቅም ያለው የፍርድ ችሎት አለላችሁ፡፡ አጥብቃችሁ በራሳችሁ ላይ ለመፍረድ ተቀመጡ፡፡ አስቀድማችሁ በደላችሁን ከፊታችሁ በመዝገብ አስቀምጡት፤ የነፍሳችሁም ወንጀል በሙሉ መርምሩ፤ ተገቢውንም ፍርድ አስቀምጡና ነፍሳችሁንይህንና ያንን በደል ያደረግሺው ለምንድነው?በሏት፡፡ ከዚህ ፈቀቅ ብላ የሌሎችን ሰዎች ኃጢአት መፈለግ ከጀመረችየተከሰስሽበት ጉዳይ የእነዚያ አይደለም፣ አንቺም የመጣሽው ስለነዚያ ሰዎች ለመሟገት አይደለም፡፡ ስለምንድነው ክፋትን የሠራሽው? ስለምንስ ነው ያንንና ይህን ጥፋት ያጠፋሽው? የራስሽን ተናገሪ እንጂ ሌሎችን አትውቀሺበሏት፡፡ ሁል ጊዜም ይህን አስጨናቂ ፈተናን እንድትመልስ አቻኩሏት፡፡ ተሸማቅቃ ምንም የምትመልሰው ነገር ከሌላትም አስፈላጊውን ቅጣት (ቀኖና) ወሱንባት፡፡ ይህን ልዩ ፍርድቤት ሁል ጊዜ የምትቀመጡ ከሆነ የእሳት ሸሎቆው፣ መርዘኛው ትልና ሊመጣ ያለውን ስቃይ በአእምሮዋችሁ እንዲቀረፅ ይረዳችኋል፡፡

ሁልጊዜምእሱ ወደ እኔ መጥቶብኝ ነው፤ እሱ ሸውዶኝ ነው፤ እሱ ፈትኖኝ ነውእያለች ከዲያብሎስ ጐን እንድትሰለፍና ሐፍረት የለሽ ንግግሮችን እንድትናገር አትፍቀዱላት፡፡ ይልቁንምአንቺ ፍቃደኛ ባትሆኚ ነው እንጂ እነዚህ ሁሉ ካንቺ ጋራ ምንም ጉዳይ የላቸውምብላችሁ ንገሯት፡፡እኔ እኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፣ የምኖረውም በምድር ነውካለቻችሁምይህ ሁሉ ሰበብና ምክንያት ነው፡፡ ብዙዎች አንቺ የለበስሽውን ሥጋ
ለብሰው በዚህች ምድር ኑረው ጻድቃንና ሰማዕታት ሆነዋል፡፡  አንቺ ራስሽ አንዳንድ ጊዜ መልካም ስታደርጊ ይኸን የምታስቢበት ሥጋ ይዘሽ ነውበሏት፡፡ ይህን ሁሉ ስትሏት በጣም ካመማት እጃችሁን አታንሱባት፡፡ ምክንያቱም (በቀኖና) ስትቀጧት ከሞት ታድኗታላችሁ እንጂ አትገድሏትም፡፡ ምክንያት የምታበዛባችሁ ከሆነምእባብ አሳተኝብላ ከተጠያቂነትና ከፍርድ ያላመለጠችውን የመጀመርያዋን ሴት እንድታስተውስ ንገሯት፡፡

ይህን ሁሉ ስታደርጉ ከአጠገባችሁ ማንም አይኑር፤  ማንምም የሚረብሻችሁ አይሁን፡፡ ይልቁንም ዳኛ በፍርድ ወንበር ላይ እንደሚቀመጥ እናንተም በፍርድ ወንበር ፈንታ በምቹ ጊዜና ቦታ በጽሞና ተቀመጡ፡፡ እራት ከበላችሁ በኋላና ወደ መኝታ ክፍላችሁ ስትሄዱ ይህን የፍርድ ወንበር ይዛችሁት ሂዱ፡፡ ነቢዩም፡- “በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ” /መዝ.44/ እንዳለው ይህ ቦታና ጊዜ ከሁሉም በላይ ተስማሚ ነውና፡፡ ይህን ዕለት ዕለት የምታደርጉ ከሆነ በዚያ በአስፈሪው የፍርድ ወንበር ያለፍርሐት ትቆማላችሁ፡፡

ሐዋርያውእኛ በራሳችን ብንፈርድ ኖሮ ባልተፈረደብም ነበር” እንዲል /1ቆሮ.1131/፡፡
ይህን ሁሉ እንድናደርግ ሰውን በመውደድ ሰው የሆነው ክርስቶስ ይርዳን አሜን!! 

1 comment:

FeedBurner FeedCount