ሓደ ሓደ ሰባት ኣዳም ካብ ገነት
ብምብራሩ ከም ቅፅዓት ጥራሕ ገይሮም ይሓስብዎ፡፡ ኣቦና ቅዱስ ኤፍሬም ወዲ ሶርያ ግና፡- “አዳም ካብ ኤደን ገነት ዝወፅአስ ብፍቕሪ
ኣምላኽ እውን ደኣ ‘ምበር በቲ ቕኑዕ ፍርዲ ኣምላኽ ጥራሕ ኣይነበረን” ይብለና፡፡ “ከመይሲ ኣዳም ምስ ኣበሰ ካብ ገነት እንተዘይባረር
ነይሩ ምስ ርስሓቱ እንዳሃለወ እታ ናይ ሂወት ኦም ምበልዐ ነበረ፡፡ እዚኣ በልዐ ማለት ከዓ ካብ ርስሓቱ እንተይፀረየ ማለት እውን
ምስ ጉድለቱ እንዳሃለወ ናብ መንግሥተ ሰማይ ምኣተወ ነይሩ፡፡ ንዘላኣለም እውን ጐዶሎ ምኾነ ነበረ፡፡ ኮይኑ ግና ጐይታ ኣፅርዩ
ከእትዎ ስለ ዝደለየ ክሳብ ባዕሉ መፂኡ ዘፅርዮ በቲ ቅኑዕ ፍትሑ ካብ ገነት አውፅኦ፡፡ ጊዜኡ ምስ በፅሐ ውን ባዕሉ መፂኡ ሥጋኡን
ደሙን ናይ ሂወት ኦም ገይሩ ሃቦ’ሞ ነቲ ብልቡ ዝሐዘነ ኣዳም ናብ ናይ ቀደም መንበሪኡ መለሶ” ይብለና!!
እሞ እቲ ፍቕሪ እግዚአብሔርስ ዋላ ኣብቲ ንዓና ሕማቕ ዝመስለና ሃዋህው እውን ምህላዉ
ኣየግርምን ዶ ትብሉ?
ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life) KEMIL BLOG YETEWSEDE Tወዳጅዋ ኦርቶዶክሳዊት ደራሲና ጋዜጠኛ ፥ ፍሬድሪካ ማቲውስ ግሪን በመጽሐፉዋ ላይ ሪቻርድ ኡምብራንድ የተባሉ የሩሜንያ የሃይማኖት መሪ ፥ በኮሚኒስት ሩሜንያ ዘመን አብረዋቸው ታስረው ስለነበሩ ኦርቶዶክሳዊ ካህን የጻፉትን ተርካ ነበር። በዚያን ወቅት የአንድ ገዳም አበምኔት የነበሩት አባ ኢስኩ በኮሚኒስቶች እጅ ብዙ ስቃይና ድብደባ ደርሶባቸው ስለነበር ከስቃዩና ከድብደባው የተነሣ ለሞት ቀርበው ነበር። ከእርሳቸው ራቅ ብሎ ደግሞ አንድ የኮሚኒስት ባለስልጣን የነበረ እንዲሁ ከደረሰበት ድብደባና ግርፊያ የተነሳ ለሞት ያጣጥራል። ሰውየው በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ አባ ኢስኩን ብዙ ስቃይና ድብደባ ያደረሰባቸው ነው፤ አሁን ግን እርሱም በተራው ከኮሚኒስት ፓርቲው ተወግዶ ለሥቃይና ለግርፋት እስር ቤት የተጣለ ነው። ነገር ግን ይህ ኮሚኒስት በዚያ ጻእር ላይ እያለ በአጠገቡ ያሉትን ሪቻርድ ኡምብራንድን ደግሞ ደጋግሞ << ይህን የመሰለ አጸያፊ ድርጊት ፈጽሜ (ንስሐ ሳልገባ) መሞት የለብኝም፥>> በማለት እንዲጸልዩለት ይነግራቸዋል።
ReplyDeleteራቅ ብለው በታላቅ ሕመም ውስጥ ያሉት ኦርቶዶክሳዊው አበ ምኔት ከተኙበት አልጋ ላይ ሆነው ንግግሩን ይሰማሉ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአጠገባቸው የሚገኙትን ሌሎች እስረኞች ግራና ቀኝ እንዲደግፉአቸው አድርገው እየተጎተቱ ያ የገረፋቸው ያ ያሰቃያቸውን ለሞት ያደረሳቸው ሰው ዘንድ ደረሱ፤ ከዚያም በአባታዊ ፍቅር ግንባሩን ዳሰሱት፤ እናም ተናገሩት፤
<< ወጣት ነህ፤ ታደርገው የነበረውን አታውቅም ነበር፤ እኔ ይቅር ብዬሃለሁ ከልቤ እወድሃለሁ፤ እኔ ኃጢአተኛ የምሆን አንተን መውደድ ከቻልኩ፥ ራሱ ፍቅር ሆኖ ሰው የሆነው ክርስቶስ ምን ያህል እንደሚያፈቅርህ አስብ። አንተ ያሰቃየሃቸው ክርስቲያኖች በሙሉ ፍጹም ይቅርታ አድርገውልሃል፥ ደግሞም ይወዱሃል፥ ክርስቶስ ይወድሃል። አንተ ደህንንነት ለማግኘት ከምትመኘው በላይ፥ ክርስቶስ እንድትድን ይወዳል። አንተ ኃጢአትህ ይቅር ይባል እንደሆነ አስበህ ይሆናል፤ አንተ ኃጢአትህ ይቅር እንዲባል ከምትመኘው በላይ ኃጢአትህን ይቅር ሊል እርሱ ይፈልጋል።አንተ ከእርሱ ጋር በሰማያት ከእርሱ ጋር ለመሆን ከምትመኘው በላይ ከእርሱ ጋር በሰማያት እንድትሆን ይመኛል፤ እርሱ ፍቅር ነው። አንተ የሚያስፈልግህ ወደ እርሱ መመለስና ንስሐ መግባት ነው።>> አሉት። ንግግራቸውን እንደጨረሱ ያ የተኛው የቀድሞ ገራፊ ኮሚኒስት በእንባና በብዙ ስቃይ ሆኖ ኃጢአቱን ሲናዘዝ፥ ገዳማዊው ኦርቶዶክሳዊ አባት ደግሞ የኃጢአት ሥርየትን ያውጁለት ነበር። ሪቻርድ ኡምብራንድ እንደነገሩን፥ ንስሐ የገባው ሰውና ኦርቶዶክሳዊው አባት በዚያው ምሽት አርፈው ወደሰማያዊ አባታቸው ዘንድ ሄደዋል።
ይህን ታሪክ ያነሳንበት ምክንያት እኒያ ኦርቶዶክሳዊ አባት ለዚያ በጸጸት እሳት ለተለበለበው ነፍስ በወቀሳ ቀስት ለተወጋው ሕይወት የሰበኩለት በመስቀል ያሸበረቀ የፍቅርና የተስፋ መልእክት፥ ዛሬም ለእኛ የመድኃኔ ዓለምን ጥንተ ስቅለቱን ለማክበር ለተሰበሰብን ሕያው የሆነ መልእክት ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር ይወደናል፤ ከታላቅ ፍቅሩም የተነሣ፥ በእኛ ፈንታ፥ ለኃጢአታችን ሥርየት ይሆን ዘንድ፥ አንድ ልጁን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል። ይህ ለእርቅ የሆነው ሞቱ ይህ ለድል አድራጊነት የሆነው የመስቀል ጉዞ የብሉይ ኪዳን መስዋዕቶችን በብዙ መንገድ የፈጸመ ስለሆነ ነው ዮሐንስ መጥምቅ << እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ>> በማለት የአዳኙን መምጣት ያወጀው። ዮሐ 1፥29 ።
..ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)...ፍርሃት የኢየሩሳሌምን ዙሪያ ገባ ከድኖታል። ምንም እንኳ የፋሲካ ሰንበት ማለትም እስራኤላውያን ከባርነት ነጻ የወጡበት መታሰቢያ የሚከበርበት ቢሆንም ከሳምንት በፊት የነበረው ስሜት የለም። ከሳምንት በፊት መሲሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቱና በውርጫው ላይ ተቀምጦ ሲገባ፥ ሕዝቡ በሙሉ ሆሳዕና በአርያም እያለ ነበር የተቀበለው፤ አሁን ግን ያ ሁሉ የለም፤ ያ ለህዝቡ የመጣው አዳኝ ተይዞ ተገርፎ ተዘብቶበት ተሰቅሎአል። መሰቀል ብቻ አይደለም ተቀብሮአል፤ ለዚያውም በእንግዶች መቃብር።
ReplyDeleteጊዜው ለርሱ ተከታዮች አስቸጋሪ ነበር። ይሁዳ ሸጠው፥ ጴጥሮስ ካደው፥ ማርቆስ ራቁቱን እስኪቀር ድረስ ልብሱን ጥሎ ሸሸ። ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ተበተኑ። ገሚሶቹ ወደ ቀደመ ተግባራቸው ማለትም አሳ ወደ ማጥመዱ፥ ወደ ቀረጡ፥ ገሚሶቹ በፍርሃት ተሸብበው በዝግ ቤት ተቀመጡ።
በሥውር ደቀ መዛሙርት የነበሩት ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጲላጦስን ለምነው የጌታን መቃብር ገነዙት፥ በአዲስ መቃብር ቀበሩት ፤ አባቶቻችን በትውፊት እንደነገሩን ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል የማይሞት የማይለወጥ እያሉ ገነዙት፤
የካህናት አለቆች እንደተሳካላቸው ቆጥረው በደስታ ሰከሩ፤ ሥጋውን ለማስጠበቅም በመቃብሩ ላይ ወታደሮችን አቆሙ።
ነገር ግን የፈሪሳውያን ጠንቃቃነት፥ የወታደሮቹ ጀግንነት የዘመናትን ምኞት፥የነቢያትን ትንቢት፥ የሱባዔውን ፍጻሜ ሊገታ አልቻለውም። ማህተመ ድንግልናዋን ሳይለውጥ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተለወለደው ጌታ በዚያ በመንፈቀ ሌሊት መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ተነሣ።
ሞት የገዛውና የሞት ምርኮኛ የነበረው የአዳም የተስፋው ፍጻሜ ከሞት ተነሣ። በክስ ወደ እግዚአብሔር ከሚጮኸው ከአቤል ደም ይልቅ የአዳምን ልጆች ኃጢአት የሚያነጻው ከሞት ተነሣ። አብርሃም በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ ያየው በግ የይስሐቅ ቤዛና ምትክ ለአብርሃም ልጆች ቤዛ ሊሆን ከሞት ተነሥቶአል።
ሀ ላንቀላፉት በኩር ሆኖ ተነስቶአል
ከሞት የተነሱ ብዙ ናቸው፤ ወለተ ኢያኢሮስ ከሙታን ተሰታለች። አልአዛር ከሞት ተነሥቶአል። ቀድሞም በብሉይ ኪዳን ብዙዎች ከሞት ተነሥተዋል። የክርስቶስን ሞት ከሌሌቹ የሚለየው በምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር፥ ምንም እንኳ
ሌሎቹ ከሞት ቢነሡም፥ የተነሡት ሞት በሚገዛው ሥጋቸው ስለሆነ ተመልሰው ሞተዋል። ክርስቶስ የተነሣው ሞት ለገዛን በሙሉ በእንዴት ያለ አኳኋን እንደምንነሳ ምሳሌ ሆኖን ነው የተነሣው። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የክርስቶስ ትንሣኤን ትርጉም በተናገረበት አንቀጽ
አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። 15 23 ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው፤
በማለት የክርስቶስ ትንሣኤ ሞትን ድል ያደረገ በአዳም በኩል ወደ ሰው ልጆች የመጣውን የሞት ፍርድ ያስወገደና በኋለኛው ዘመን የሚሆነውን የሙታን ትንሣኤ ያስረገጠ እንደሆነ በመግለጥ ይህ የክርስትናችን ታላቅ ተስፋ እንደሆነ ገልጦአል፤ 1 ቆሮ 15፥21-23።
ዮሐንስ ወንጌላዊ ከሐሙስ ማታ ጀምሮ የተከናወነውን አስደናቂ ክንውን የገለጠው በሚያስደንቅ መንገድ ነው።
ReplyDeleteኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው። ዮሐ 13፥1
የወደዳቸውን እስከመጨረሻ ወደዳቸው። ምንኛ አስደናቂ አነጋገር ነው። ጌታችን የተቀበለው መከራ ድንገት የሆነ ሳይሆን በፍቅር የሆነ ነው። በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ ፍቅር! መለኮታዊ ፍቅር!
ጴጥሮስ እንደሚክደው፥ ይሁዳ እንደሚሸጠው ፥ ደቀመዛሙርቱ እርሱን ጥለው እንደሚሸሹ እያወቀ የወደዳቸውን እስከመጨረሻ ወደዳቸው።
ግሩም በሆነው በጸጋው ዙፋን ፊት በድፍረት እንድንቀርብ ድፍረት የሚሆነን ይህነው። የወደደን ያለምንም ምክንያት ነው። የወደደን ወሰን በሌለው ፍቅር ነው። ኦ ለዚህ ወሰን ለሌለው ፍቅር አንክሮ ይገባዋል።
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይህን ፍቅርህን ዕለት ዕለት ግለጥልኝ። ለእኔ ያለህ ፍቅር ወሰን የሌለው ቢሆንም እኔ ግን ውሱን በሆነው የዓለም ፍቅር እየተንገገላታሁ ነኝና።
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ ያሳየኸኝን ድንቅ የሆነውን ትህትናህን እንዳልረሳው አሳስበኝ። ሽርጥ ታጥቀህ የደቀመዛሙርትህን እግር ያጠብከው ይህን ልታስተምረኝ ነውና።
አምላኬ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ህይወቴን በፍቅርህ ሙላው በጸጋህ እጠበኝ።
በመስቀል ላይ እንዴት እጅህን ዘረጋህ እንዴትስ በቀኖት ተቸነከርክ? ወዴትስ ወረድክ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፍቅርህን በልቤ ውስጥ ቅረጽ ከክፉ ማሰሪያ ፍታኝ፤ ለዘላለም በሚኖረው ፍቅር እሰረኝጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማሕየዊ መስቀልህን አቅፌ ከእርሱ የሕይወትና የመድኃኒት መዐዛ እንዳሸት አድርገኝ፤በልቡናዬም ውስጥ ንጹሕ ደምህ ይውረድ ንጹሕ መሠዊያ ይሆን ዘንድ ልቡናዬን ያክብረው፤ በውስጡም የሕይወት መንፈስ ይንቀሳቀስ፤ የሕይወትንም መንፈስ አንተን ይቀበል።ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life).
ReplyDeletekale hiwot yasemalen
ReplyDeleteበቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ReplyDeleteለዚህ ታላቅ ፍቅር አንክሮ ይገባል፡፡ ከእግዚብሔር ዘንድ ለሰው ወገን ለተደረገ ለማይመ ረመር ፍቅሩ አንክሮ ይገባል፡፡ ይህ ለመላእክት ያላደረገው ነው፡፡ የተነገረውን አስተውል፣ እግዚብሔር ከእኛ ባሕርይ የተዋሐደው ተዋሕዶ ጥቂት ክብር አይምሰልህ፡፡
ይህን ለመላእክት አላደረገውና!! የመላእክት ባሕርይም አልተዋሐዳቸውምና የተዋሐደችው የኛ ባሕርይ ናት እንጂ፡፡ባሕርያችንን ተዋሕዶአል እንጂ ከባሕርያችን ከፍሎ ተዋሐደ ለምን አላለም? ወዳጁ እንደ ኮበለለ እስኪያገኘውም ድረስ እንደ ሔደና እንደአገኘው ሰው የእኛ ባሕርይ እንደዚህ ከእግዚብሔር ተለይታ ነበርና ከእርሱም ፈጽማ ርቃ ነበርና ሥጋ በመሆን ገንዘብ እስኪያደርጋት ድረስ ፈጥኖ ፈለጋት እርሷም ተዋሐደችው ይህንንም ተዋሕዶ እኛን በመውደድ እንዳደረገው የታወቀ ነው፡፡
ለማይደፈር ለዚህ ድንቅ ምስጢር እንክሮ ይገባል!! ከእግዚብሔር ጋር አንድ በመሆን የሚኖር መላእክትና የመላእክት አለቆች ሱራፌልና ኪሩቤል የሚሰግዱለት ሥጋ ከእኛ ባሕርይ ይገኝ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ አንድነት አለን? ዕብ1፡ 3-8፡፡
ይህን መላልሼ ባስብሁት ጊዜ ሰው ያገኘው ልክ መጠን የሌለውን ፍፁም ክብር፡ ከእግዚአብሔር የተደረገውን፡ ባሕርያችን ያገኘውን ታላቅ ፍቅር አይቼ ከዚህ የተነሣ አደንቃለሁ፡፡ስለዚህም ወንድሞቹን /ደቂቀ አዳምን/ በሁሉ ይመስላቸው ዘንድ ይገባል አለ!! ሁሉ ያለው ምንድን ነው፡ እንደ እኛ ፍጹም ሰው ሆኖ መወለዱ፣ ከኃጢአት ብቻ በቀር እንደ እኛ ለሥጋ የሚስማማውን ሁሉ መሥራቱም ነው እንጂ ይኸውም በፈቃዱ ያደረገው መፀነስ፣ መወለድ፣ መብላት፣ መጠጣት፣ መተኛት መድከም፣ መታምና መሞት ነው፡፡
የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ,,,, ክርስቶስን ትለብስ ዘንድ በውኃ ስሙን እየጠራህ ተጠምቀሃል፡፡ በጥምቀትም የጌታህ ዙፋን አካልህ እንደሆነ ማኅተሙም በግንባርህ ላይ እንደታተመ ልብ በል፡፡ ከእንግዲህ አንተ የሌሎች ሌሎችም የአንተ ጌቶች አይደሉም የጌታ እንጂ፡፡
ReplyDeleteበርህራሄው ዳግም የፈጠረን ጌታ ኢየሱስ አንድ ነው፡፡ በመስቀሉ ላይ በፈፀመው ቤዛነት በኩል እኛን ያዳነን እርሱ አንድ ነው፡፡ ሕይወታችንን በጽድቅ የሚመራት እርሱ ብቻ ነው፡፡ ትንሣኤያችንን የሚፈጽምልን እርሱ ነው፡፡ እንደ ሥራችንም ዋጋችንን የሚከፍለን እርሱ ነው፡፡ በሥራዎቹ ቸርና ሩህሩህ የሆነውን አባት እንዳታስቆጣው፡፡
በባልንጀራህ ላይ የምትቆጣ ከሆነ የአንተ ቁጣ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ ቂምን በልብህ የያዝክ ከሆነ ቂምህ በጌታ ላይ ነው፡፡ ባልንጀራህን በከንቱ የምትቆጣው ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ ይስለጠንብሃል፡፡ ልብህን የፍቅር ማደሪያ ካደረከው በምድር ላይ አንዳች ጠላት አይኖርህም፡፡
አምላክህ ክርስቶስ ስለ ገዳዮቹ በመስቀሉ ላይ ሳለ ይቅርታን ለመነ፡፡ እንዴት አንተ ፍጥረትህ ከትቢያ የሆነ ቁጣን በፈቃድህ በራስህ ላይ ታቀጣጥላለህ? አንተ በክርስቶስ ደም ወደ እርሱ ቀርበሃል፤ በሕመሙም ድነሃል፡፡ በአንተ ፈንታ ለኃጢአት ስራዎችህ ምትክ ሆኖ ስለ አንተ መተላለፍ እርሱ ሞቷል፡፡ አይሁድ በመዘበት በፊቱ ላይ ምራቃቸውን ሲተፉበት መታገሱ ሰዎች ቢያፌዙብህ እንኳ እንድትታገሳቸው አርአያ ሊሆንህ ነው፡፡ መራራና ሆምጣጣ የሆነውን ወይን መጎንጨቱ ከቁጣ ትሸሽ ዘንድ ነው፡፡ በጅራፍ ተገርፎ፣ በሰንሰለት ታስሮ መጎተቱ ስለ ጽድቅ ስትል መከራን እንድትቀበል ነው፡፡
Dear Anonumous! Kalehiwet yasemaln! If you contact me through my email or FB addres, so that we can work together in Mekrez. Pls pls pls!
ReplyDeletewendeme ene endmetasbegh awaki weyim yetmarku yebetkrstian sew aydelehum gena yehikemna(medicine) yesostegha(3rd) amet ye univesity temari negh ahunem betmhert lay negh beterefe gin ketelyayu orthodoxawi website yageghochewen tiru tshufoch lemakafel zigju negh
ReplyDelete