Wednesday, August 8, 2012

የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ!


 ክርስቶስን ትለብስ ዘንድ በውኃ ስሙን እየጠራህ ተጠምቀሃል፡፡ በጥምቀትም የጌታህ ዙፋን አካልህ እንደሆነ ማኅተሙም በግንባርህ ላይ እንደታተመ ልብ በል፡፡ ከእንግዲህ አንተ የሌሎች ሌሎችም የአንተ ጌቶች አይደሉም የጌታ እንጂ፡፡
በርህራሄው ዳግም የፈጠረን ጌታ ኢየሱስ አንድ ነው፡፡ በመስቀሉ ላይ በፈፀመው ቤዛነት በኩል እኛን ያዳነን እርሱ አንድ ነው፡፡ ሕይወታችንን በጽድቅ የሚመራት እርሱ ብቻ ነው፡፡ ትንሣኤያችንን የሚፈጽምልን እርሱ ነው፡፡ እንደ ሥራችንም ዋጋችንን የሚከፍለን እርሱ ነው፡፡ በሥራዎቹ ቸርና ሩህሩህ የሆነውን አባት እንዳታስቆጣው፡፡
በባልንጀራህ ላይ የምትቆጣ ከሆነ የአንተ ቁጣ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ ቂምን በልብህ የያዝክ ከሆነ ቂምህ በጌታ ላይ ነው፡፡ ባልንጀራህን በከንቱ የምትቆጣው ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ ይስለጠንብሃል፡፡ ልብህን የፍቅር ማደሪያ ካደረከው በምድር ላይ አንዳች ጠላት አይኖርህም፡፡
አምላክህ ክርስቶስ ስለ ገዳዮቹ በመስቀሉ ላይ ሳለ ይቅርታን ለመነ፡፡ እንዴት አንተ ፍጥረትህ ከትቢያ የሆነ ቁጣን በፈቃድህ በራስህ ላይ ታቀጣጥላለህ? አንተ በክርስቶስ ደም ወደ እርሱ ቀርበሃል፤ በሕመሙም ድነሃል፡፡ በአንተ ፈንታ ለኃጢአት ስራዎችህ ምትክ ሆኖ ስለ አንተ መተላለፍ እርሱ ሞቷል፡፡ አይሁድ በመዘበት በፊቱ ላይ ምራቃቸውን ሲተፉበት መታገሱ ሰዎች ቢያፌዙብህ እንኳ እንድትታገሳቸው አርአያ ሊሆንህ ነው፡፡ መራራና ሆምጣጣ የሆነውን ወይን መጎንጨቱ ከቁጣ ትሸሽ ዘንድ ነው፡፡ በጅራፍ ተገርፎ፣ በሰንሰለት ታስሮ መጎተቱ ስለ ጽድቅ ስትል መከራን እንድትቀበል ነው፡፡ 
(ምንጭ፡- ስብከት ወተግሳጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም፣ በመ/ር ሽመልስ መርጊያ፣ ገጽ 65-66)

13 comments:

  1. kale hiyiwet yasemalin tiru tsuhufi new ayayizewim suhufu yetegegnebet minichu bitekesi melikam yimesilegnal

    ReplyDelete
  2. betelhemm blogspot.com yageghehut new adrashawn balemetkese yikerta

    ReplyDelete
  3. tshufu ke decon shimeles mergiya ,metshaf yetewsede new yemtshafu sem ,sebket wetegtsats be kidus eferem

    ReplyDelete
    Replies
    1. melikam memihi edih minichu sitekes anibabi bekelalu anibibo medat edichili yiredwal bemili eminete new Egiziabihar yakibilin egiziabihari yisitilin .

      Delete
  4. ስንዱ…AGERE ETHIOPIA

    ጥበብ፡ በድንኳንሽ፡ ያደረ፣
    ዋጋሽ፡ ከእንቁ፡ የከበረ፣
    ክንድሽ፡ ለትጋት፡ የበረታ፣
    እጅሽ፡ ለድሀ፡ የተፈታ፣
    ጣቶችሽ፡ እንዝርት፡ ይዘው፡ ዘርፍ፡ የቋጩ፣
    ቤቶችሽ፡ በጽዮን፡ ሸማ -
    በእጥፍ፡ ድርብ፡ ነጠላ፡ የታጩ።
    ስጋጃን፡ በእልፍኝሽ፡ ሠርተሽ፣
    የበፍታን፡ ቀይ፡ ግምጃ፡ የለበስሽ፣
    አንደበትሽ - በርኅራኄ፡ ህግ፡ የተገራ፣
    ጥበብን፡ በማለዳ፡ የጠራ።
    ልጆችሽ፡ ባንቺ፡ ብርታት ፣
    በማለዳ፡ ተነስተው፣
    ጥበብን -
    በአንደበታቸው፡ ጠርተው፣
    የድግሽን፡ ሽያጭ፡ እየመነዘሩ፣
    በሸንጎ -
    ሥራሽን፡ ለብዙ፡ ዘመን፡ አወሩ።
    ስንዱ፦
    ቀን፡ አለፈ፣
    ምሽት፡ ከምሽት፡ ጀርባ፡ ተሰለፈ።
    ሆነ፡ ማታ፣
    እንደገናም፡ ምሽት፣
    ጽኑ፡ ጨለማ፡ ውድቅት።

    ውድቅትነቱን፡ አይታ ፣
    መመሳሰልን፡ አጥንታ ፣
    ነፍሳትን፡ በጎዳና፡ ልታጠምድ፣
    ያዘጋጀች -
    የሚያዳልጥ፡ ብዙ፡ መንገድ፣
    ከንፈሯ፡ ልዝብ፡ የማያፍር፣
    ጨዋታዋ፡ ስሜትን፡ የሚያሰክር ፣
    ቀበዝባዛ፣
    የምታምር፡ ጋለሞታ ፣
    ከባቢሎን፡ ተነስታ፡ መጥታ ፣
    ከጎበዛዝት፡ መካከል፡ ገብታ ፣
    ባልጋዋ፡ ሰርፍ፡ ዘርግታ ፣
    አልሙና፡ ቀረፋም፡ ረጭታ ፣
    የመውደድ፡ በሚመስል፡ ፈገግታ ፣
    በጎዳና -
    በየማእዘኑም፡ ጎትጉታ ፣ ጎትጉታ፣
    በተሳለ፡ ምላስ፡ ወግታ ፣
    ብላቴኖችሽን፡ በልታ፣ በልታ ፣
    ቆላዎችሺን፡ ከደጋ፣
    ባህሮችሽን፡ ከተራሮችሽ፡ ለይታ፣
    ዙፋን፡ የጋራ፡ እንጂ፡ የውድሽ፡ አይሆንም፡ ብላ፣
    እጅ፡ መንሻ፡ ጥላ፣
    ጎበዛዞችሽን፡ ሸንግላ፣
    ከመኳንንቶችሽ፡ ሰፈር፡ ገብታ፣
    ምርጦችሽን፡ አስታ፣
    የተቀደሰውን፡ አርክሳ፣
    ላንቺም፡ መቃብር፡ ምሳ፣
    ወንዞችሽን፡ አድርቃ፣
    ዛፎችሽን፡ አጠውልጋ፣
    ለባቢሎን፡ ርስት፡ ፈልጋ፣
    ዘርግታለችና -
    ምላሷን፡ እስከ፡ ውድሽ፣
    ድንኳኗን፡ እስከተራሮችሽ።
    ስንዱ፡-
    ስጋጃሽን፡ በእልፍኝሽ፡ አንጥፊና፣
    የቀይ፡ ግምጃ፡ ልበሽና፤
    ሸማሽን፡ አጣፊና፣
    ዙፋኑን፡ አዘጋጅተሽ፡ እንደድሮው፤
    በማለዳ፡ ጥበብን፡ ጥሪው፣
    ውድሽን፡ ና ፦
    እርስትህን፡ አድን፡ በይው።
    ከባቢሎን፡ የመጣችው፣
    መግቢያ፡ መውጫየን፡ የዘጋችው፣
    የእልፍ፡ አእላፍን፡ የለት፡ መስዋእት፡ ያስቀረችው፣
    ከቆምክበት፡ ቆማ፣
    ቀንበር፡ በልጆቼ፡ ጭና፣
    ርስትህን፡ ሺታለችና፣
    አቅምም፡ ከልጆቼ፡ ሸሽቷልና፣
    ላንተ፡ የሚሳንህ፡ የለምና፣
    በይው፦
    ውዴ፡ ና፣ ቶሎ፡ ና

    ReplyDelete
  5. le islam tiyake mels yemihon tshufm bittsef tiru new ke dekike nabute.blogspot yetewsede tshuf bemasnebeb lejemrlh ante ketlbet ለምን አልሰለምሁም? ክፍል ሁለት ምሥጢረ ሥጋዌ

    ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ በሰፊው ለክርስቲያን በብዙ ቦታዎች ተጽፎል፡፡
    ለነዲዳትና ለመሰሎቹ በመልስና በመረጃ መልክ ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ በአጭሩ ተገልጧል፡፡

    እሱም በመጀመሪያ የኦሪትን ከዚያ የቁርአንን ስለአዳም መውደቅ ታሪክ መነሻ አድርጎ .....ታትቷል፡፡....yiketlal
    (ዘፍ 2፡7) ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት አፈር ወስዶ፣ ሰውን ከአፈር አበጀው፣ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፡፡ ሰውም ሕይወት ያለው ፍጡር ሆነ፡፡
    (ዘፍ 2፡15)ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በኤደን የአትክልት ቦታ አኖረው፤ይህንም ያደረገው ሰው የአትክልቱን ቦታ እንዲያለማውና እንዲኩተኩተው ነው፤ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በአትክልቱ ቦታ ከሚገኙት ዛፎች ሁሉ ፍሬ ብላ፤ ነገር ግን ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት ከሚሰጠው ዛፍ ፍሬ አትብ፤ ምክንያቱም ከዚህ ፍሬ በበላህበት ቀን በርግጥ ትሞታለህ ብሎ አዘዘው፡፡
    (ዘፍ 2፡18) እግዚአብሔር አምላክም አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፡፡ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት፡፡
    (ዘፍ 2፡20) ----- ፤ እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅለፍን ጣለበት አንቀላፋም፣ ከጎድኑም አንዲት አጥንት ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ሞላው፤ እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት፣ አዳምም ይህች አጥንት ካጥንቴ፣ ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል፡፡ ስለዚህ ሰው አባትና እናቱን ይተዋል፣ ከምሽቱም ይጣበቃል፤ ሁሉም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፡፡ አዳምና ምሽቱ ሁለቱም ዕራቁታቸውን ነበሩ፡፡ አይተፋፈሩምም ነበር፡፡
    (ዘፍ.3፡1……፣)አዳምና ሔዋንም በዚህ ሁኔታ በገነት መካከል የፍጥረታት ሁሉ ገዥዎች ሁነው ሲኖሩ ሰይጣን ቀናና በእባብ ተመስሎ የተከለከለችውን ዕፅ እንዲበሉ በማድረጉ የአምላካቸውን ትእዛዝ በመተላለፋቸው ተረግመው ከገነት ወጡ፡፡
    ይህ ታሪክ በቁርአን ደግሞ እንዲህ ነው፤ (ላሟ ምዕራፍ ፡2፡34-38) መላእክትንም ለአዳም ስገዱ ባልነ ጊዜ ከዲያብሎስ በቀር ሁሉም ስገዱ፣ እሱ ግን እምቢ አለ፣ ኮራም በዚህም ከከሐዲዎች ተቆጠረ አዳም ሆይ !አንተ ከነምሽትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ስፍራ በሰፊው ተመገቡ፣ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትሆናላችሁና አልነም፡፡ ከርሷም ሰይጣን አዳልጦ (አሳስቶ) በውስጡ ከነበሩበት ድሎት አወጣቸው፡፡ አንዱ ለሌላው ጠላት ሁናችሁ ውረዱ፣ ለእናተም በምድር ላይ እስከ ጊዜያችሁ ድረስ መጠለያና ሥንቅ አለላችሁ፡፡ በኦሪትም ሆነ በቁርአን እግዚአብሔር ትእዛዙ በመጣሱ አዝኖ አዳምና ሔዋንን ከገነት እንዳስወጣቸው ቁልጭ ተደርጎ ተጽፏል፡፡ ቁርአን ከዚህ በኋላ ስለመታረቅና ድኅነት የሚናገረው የለም፣ ከአሕዛብ ልማድ ከመጣው መሥዋዕተ እንስሳ በቀር፡፡ ኦሪትና ወንጌል ግን በትንቢትና በፍጻሜ አምላክ ዓለምን የታረቀው በልጁ ደም መሆኑን አብራርተው፣ ነግረው ደምድመዋል እዳም የፈጣሪውን ትእዛዝ በመተላለፍ ከገነት ወጥቶ፣ እሱ ብቻ ሳይሆን በመላ ዘሩም በምድረ ፋይድ ሲኖር በሦስት አካላት ሲመሰገን የሚኖር እግዚአብሔር በዳዩን አዳምን ይቅር ለማለት ወሰነ፡፡(ዘፍ.3፡1-4) ለዚህም መታረቂያ መሥዋዕት አስፈለገ፡፡ በደሉም ግዙፍ ስለሆነ ለመሥዋዕቱ የሰውና የእንሰሳ ደም የማይበቃ ሆነ፡፡ የስላሙ የመሐመዱ፣ የቁርአኑ አምላክ ቢሆን ኑሮ ያፍርድ እንደ ዐጤ ስለሚሰራ ምሬሃለሁ ቢል ይበቃ ነበር፡፡ የአብርሃም አምላክ ግን እውነተኛ ዳኛም መሓሪም ስለሆነ፣ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው ልጁ ሥጋ ለብሶ እንዲሠዋ ወሰነና ላከው፡፡ (ዘፍ.3፡15) በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አኖራለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ ባለው መሠረት፣ በዳይም ተበዳይም ልጅ ልጃቸውን አዋጡና የአምላክ ልጅ እግዚአብሔር ወልድ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ፣ሥጋ ለብሶ፣ ትስብአርትን ተዋሕዶ የሰውን ልጅ ጠላት ሰይጣንን ድል ነሥቶ ፣ ከዲያብሎስ ባርነት ከሲኦልና ከገሃነም ሥቃይና ኩነኔ አዳነ፡፡ የተበዳይና የበዳይ ልጅ (ዘር) በተዋሕዶ ሥጋ ተሰቅሎ ዓለምን አዳነ፡፡ ከሦስቱ ሥላሴ፣ ከሠለስቱ አካላት አንዱ በተለየ አካሉ እግዚአብሔር ወልድ ሥጋ ለብሶ፣ ተሠቃይቶ፣ ተገፎ፣ ተገርፎ፣ ተሰቅሎ ዓለምን እንዲያድንና ከአባቱም ከራሱም ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ እንደያስታርቅ እንዴት እንደ ተወሰነ በሥሉስነት ሲመሰገን ከሚኖረው ከገናናውና ከረቂቁ አምላክ አንዱ እግዚአብሔር በቀር ማንም አያውቅ፡፡ ተበዳዩ አምላክ በዳዩን ሰውን ይቅር የሚልበት ጊዜ ሲደርስ፣ በመበሠሩ በቅዱስ ገብርኤል አማካይነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያምን ይሁን ይደረግልኝ ፈቃድ ብኋላ፣ አንድያ፣ ተቀዳሚ፣ ተከታይ የሌለው ልጁን ሥጋ እንዲዋሃድ እንዲለብስ ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ላከ፡፡


    በልደት ሦስቱም፤ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ተስማምተዋል፣ ተባብረዋል፡፡ አብ መርጧል፣አጽንቷል፤ መንፈስ ቅዱስ በላያዋ ላይ አድሮ ወላዲተ አምላክ ማኅደረ መለኮት እንድትሆን አመቻችቷል፣ አዘጋጅቷታል፡፡ እግዚአብሔር ወልድም ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ ፍጹም ሰው ሁኗል፡፡ ስለዚህም በአንድ አካል የተዋሐደ ሰውና አምላክ ይባላል፡፡ ስለዚህም በአንድ እረኛ አንድ መንጋ በተሰጠው ውሳኔ አንድ መለትስ ይባላል፤ (መለትስም ሰውና አምላክ ወይም መለኮትና ትሰብእት ማለት ነው) በመለኮቱ የአብ ልጅ፣ በትስብእቱ (ሥጋው) የማርያም ልጅ ይሉሃል ይህ ነው፡፡ በግዕዙም ወልደ አብ በመለኮቱ ወልደ ማርያም በትስብእቱ ይላል ውሳኔው፡፡ ሰው አምላክ፣ አምላክ ሰው ሆነ የሚያሰኘውም ይህ ነው፡፡ በመለኮቱ አምላክ አማልክት፣ ፈጣሬ ዓለማት ሲሆን፣ በትስብእቱ ደግሞ ንጉሠ ነገሥት፣ ሊቀ ካህናት፣ ሊቀ ሰማዕት፣ ሊቀ ነቢያት ነው፡፡ እንደ ሰውነቱ፣ ሰው መሆኑን ለማጠየቅ ትንሽ በትንሽ አድጓል፣ እንደ ሕፃናት አልቅሷል፣ደክሟል፣ ተርቧል፣ ተጠምቷል፣ ምራቅ፣ ደም ወጥቶታል፣ ሙቷል፡፡ አምላክ እንደ መሆኑ፣ አምክነቱን ለማጠየቅ (ለማስረዳት) በድንግልና ተወልዷል፣ በተዘጋ ቤት ገብቷል፣ በባሕር ላይ ያለ ጀልባ ሂዷል፤ ከሞተና ከተቀበረ በኋላ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ተነሥቷል፤ በዚህም አንደ መለትስነቱን እነረዳለን፡፡መለትስ መሆኑን ያልተረዱ ብዙ ሰዎች ትስብእትን ሲያይ የተነገሩትን ቃላት፣ ጥቅሶች፣ ዐረፍተ ነገሮች፣ ባነበቡ ቁጥር ለማረም ወይንም ለማጣመም ይሞክራሉ፡፡ ይህ ግን ካለማወቅ የመጣ ነው፤ ልኩ መለኮቱነ ሲያዩ የተነገሩትን ለመለኮቱ ሰጥቶ በመለኮት ባሕርይ መተርጎም፣ በትስብእት፣ ለትስብእት የተነገሩትን ደግሞ ለትስብእት ሰጥቶ ከነበቡ በኋላ አንድ አካል አንድ መለትስ ብሎ አስታርቆ አስማምቶ መፍታት ነው፡፡

    ReplyDelete
  6. ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ወልድ የአብና የማርያም ልጅ፣ በአንድ መለትስ መሆኑን ለመረዳት በሰፊው የሚፈልግ ሁሉ ወደ ፊት በሌሎች ክፍሎች የምናየው ይሆናል፡፡ ከዚህ ግን ፍጽም አምላክ እና ፍጹም ሰው በአንድ አካል እንድመለትስ መሆኑን ለማስረዳት የሚከተሉት ተጠቅሰዋል፤ (ዮሐ.1፡1-14) 3፡1618፤ መዝ.2፡68፤ 109፡4፤ ሉቃ.23፡34፤ ዮሐ.10፡30፤14፡6፤20፡17፤ ኢሳ.61፡13፤ ሉቃ.418-19፤53፡11-12፤ ዮሐ.14፡28፤31፤ መዝ. 21፡1፤ ማቴ.27፡46፤ ሉቃ.13፡32፤ 2ቆሮ.1፡3፤11፡31፤ ኤፌ.1 ኢሳ.3፤17፤ ፊል.2፡6፣10፤ 1ጴጥ.1፡3፤ 2ጴጥ 1፡17-18፤ ግብ.ሐዋ 2፡24፤ ራእ.1፡6፤3፡12 ዮሐ.6፡37-39፤7፡29፤ 1፡36፤8፡42፤9፡4፤ ሉቃ.4፡43፤ ገላ.4፡4፤ ዮሐ.4፡9) ከቅዱሳት መጻሕፍት አምላክና ሰው መሆኑን ለመግለጥ የተጻፈ ለቁጥር የሚዳግቱ ብዙ ጥቅሶች አሉ፡፡ቁርአንም የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ያምናል፤ ይህንም
    በምስጢረ ሥላሴ ከዚህ በፊት በክፍል አንድ ላይ አስረድተናል፡፡ ከዚህ ደግሞ
    ሀ. (ሱራህ. 19፡17-22፤) ማርያምን ከቤተሰብዋ ወደ ምሥራቃዊው ክፍል በተነሣች ጊዜ በተገለለች ጊዜ አውሣ፡፡ መንፈሳችንንም ወደ እሷ ላክን፤ እሱም ፍጹም ሰው መስሎ ታያት፡፡ እስዋም እኔ ከእንተ በጌታ እጠበቃለሁ፣ ጌታህን ፈሪ እንድሆን አለችው፡፡ እሱም እኔ ንጽሕን ልጅ ለአንቺ ልስጥሽ ከጌታሽ የተላክሁ ነኝ አላት፡፡እሷም ወንድ ሳይነካን አመንዝራም ሳልሆን እንዴት እወልዳለሁ አለቸው፡፡ እሱም ጌታሽ ይህ ለኔ ቀላል ነው፤ እኛ ለሰው አስተርእዮና የኛንም ምሕረት መግለጫ እናደርገዋለን፣ ይህም የተወሰነ ነው ይላል፡፡ እስዋም ፀነሰችው ወደ ሩቅ ቦታም ሽሽች፡፡
    ሊ (ሱራህ፡2፡253) ከእነዚህ መልእከተኞቻችን ግማሹን ከሌሎች በላይ አበለጥን፡፡ እኩሎቹን አላህ አነጋገራቸው፣ ሌሎችን ደግሞ በደረጃ ሱራህ፡19፡) አበለጣቸው፡፡ ለማርያም ልጅ ኢየሱስ ግን የአምክነቱን ግልጽ ምልክት (ተአምር) ሰጠነው፤ በመንፈስ ቅዱስም አበረታነው፡፡
    ሐ, (ሱራህ፡ 3፡ 45-48) መላእክት ያሉትን አስታውሥ፤ማርያም ሆይ! አላህ ከርሱ በሆነው ቃል፣ ስሙም ኢየሱስ ክርስቶስ የማርያም !ልጅ የሚባል፣ በዚህ ዓለምና በመጭው ዓለም ከባለሟሎቹ ሁሉ የከበረ ልጅ ሲሰጥሽ የምሥራች ይልሻል (ያበሥርሻል) እሷም ጌታዬ ሆይ! ሰው ሳይነካኝ ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንደዚህ ነው፣ አላህ የሚሻውን ያደርጋል፤ አንዳችን ነገር በሻ ጊዜ፣ ሁን ይለዋል ወዲያውም ይሆናል፡፡ ብራና ባይወደድ ኑሮ ቁርአን መደጋገም ልማዱ ስለሆነ ብዙ መጥቀስ ይቻላ፡፡
    ከዚህ የተረፈውን ክርስቶስ ፍጽም አምላክ ፍጹም ሰው ነው በሚሉት አርእስት ይመለከቷል፡፡
    ወስብሃት ለእግዚአብሄር
    ይቆየን ይቀጥላል
    በተከታታይ በክፍል በክፍል የምናቀርብላችሁ ይኖራል ተከታተሉን
    ምንጭ፡ ለምን አልሰለምሁም ገፅ 16-19

    Posted by ደቂቀ ናቡቴ at 12:49 AM

    ReplyDelete
  7. በምስጢረ ሥላሴ አካል ለቀዋሚ ነገር ለመንፈስ ነው የሚነገረው፤ አይታይም አይዳሰስም፤ መንፈስ ነው፡፡ ስለዚህ ነው ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ በተለየ ረቂቅ አካሉ ሥጋ ስለለበሰ። ሰውነት(የሚዳሰስ አካል) አለው የሚባለው፡፡ ባሕሪያቸው መለኮታቸው፣ መንግሥታቸው፣ ሥልጣናቸው ግን አንድ ነው፡፡ በአካል ሦስት ስለሆኑና በመለኮት፣ በባሕርይ አንድ ስለሆኑ፣ እኔ እያለ በነቢያት በክርስቶስ፣ በሐዋርያት፣ እግዚአብሔር ሲያናግር ኑሯል፡፡
    (ዮሐ. 1፡1-3) በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ይህ በመጀመሪያ በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፡፡ ሁሉም በእሱ ሆነ፡፡ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ የሆነ የለም። ከዚህ ላይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእግዚአብሔር አብ ጋራ ሌላ እግዚአብሔር ወልድ እንዳለ እና ያለእሱም ምንም እንዳልሆነ ይናገራል፤ በአካል የተለያዩ በመለኮት ግን አንድ የሆኑ፤ ሁለት አካላት፤ አንድ እግዚአብሔር እንድ እግዚአብሔር እንዳለ ወንጌላዊው ቁልጭ አድርጎ ገልጧል፤ ከዚህ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ አካላት አብና ወልድ ናቸው፣ ዝቅ ስንል ደግሞ ሦስት አካላት መሆናቸውን እናያለን፡፡
    (ማቴ.3፡16-17) ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኋ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ወርዶ ከእሱ ላይ ሲቀመጥ አየ፡፡ እነሆም ድምፅ ከሰማይት ወጥቶ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ፡፡ በዚህም በአምሰላ ርግብ የወረደው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፤ የምወደው ልጄ ያለ እግዚአብሔር አብ ፤ ተጠማቂው ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ በትስብእቱ ዐማኑኤል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባለው፣በኋላ የቤተክርስቲያ ሊቃውንት ሥላሴ ብለው የሰየሟቸው አካላት፣ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡(ማር.1፡911፤ ሉቃ.3፡21-22)
    ይኽው ታሪክ በድብረ ታቦርም ተደግሟል፣ ያውም ከትእዛዝ ጋራ፣ (ማቴ.17፡1-6፤ማር.9፡2-13 ሉቃ.9.28-36)"እነሆም ከደመናው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት፡፡"፥
    (ዮሐ.11፡4) ኢየሱስም ሰምቶ፣ ይህ ሕመም የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ይከብር ዘንድ ስለ እግዚአብሔር ክብር ነው እንጂ ለሞት አይደለም አለ፡፡
    (ዮሐ.11፡-፡27) አዎ!ጌታ ሆይ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ቁርአንና እስላሞች እንደሚሉት አምላክ ባይሆን ኑሮ፣ አይደለሁም ተሳስተሸል፣ እኔ አምላክ አይደለሁም ይላት ነበር፡፡
    (ዮሐ12፡45) " እኔን ያየ የላከኝን አየ፡፡" ከዚህም ላኪና ተላኪ ሁለት አካል መኖራቸውን ይናገራል፡፡
    (ዮሐ13፡3) ኢየሱስ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው ከእግዚአብሔርም እንደመጣ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ዐውቆ ከእራት ተነሥቶ ልብሱን አኖረ፡፡
    (ዮሐ14፡1) ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔርም እመኑ፣ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ---፡፡
    ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት፣ ሕይወትም ነኝ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡ እኔንስ ብታወቁኝ አባቴንም ደግሞ ባወቃችሁ ነበር፡፡
    (ዮሐ14፡15-17) ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ፡፡ እኔም አብን እለምነውዋለሁ፣ ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላውን አጽናኝ እንዲሰጣቸሁ። እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ሰላሆነ ሊቀበለው የማይችል የእውነት መንፈስ ነው፤ እናንተ ግን ከእናንተ ዘንድ በውስጣችሁም ስለሚኖርታውቁታላችሁ፡፡ በዚህም ሦስት መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አብን እለምነዋለሁ፤ መንፈስ ቅዱስ ይልክላችኋል ብሎ ፣ሦስቱንም፤ ተለማኝ ፣ ለማኝ ፣ተላኪ አድርጎ ሦስቱን አካላት ዘርዝሯል፡፡
    (ዮሐ14፡23-24) ኢየሱስም መልሶ አለው፣ የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፣ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን፡፡ የማይወደኝም ቃሌን አይጠብቅም (እንደአይሁድና እንደ አሕመድ ዲዳት ያለው)፡፡ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እጂ የኔ አይደለም፡፡
    (ዮሐ14፡25) ከእናንተ ጋራ ስኖር ይህን ነገርኋችሁ፣ አብ በእኔ ስም የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፣እኔ የነገርኋችሁንም ሁሉ ያስተውሳችኋል፡፡
    (ዮሐ14፡31) ነገር ግን እኔ አብን እንደምወደው ዓለም ያውቅ ዘንድ አብ ያዘዘኝን ሁሉ እፈጽማለሁ፡፡
    (ዮሐ.15፡9) አብ እኔን እንደ ወደደኝ እኔም እናነተን ወደድኋችሁ፡፡ (15) አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፡፡ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለነገርኋችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፡፡
    (ዮሐ.15:21) የላከኝን ስለማያውቁ በእኔ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል፡፡
    (ዮሐ.15:23) እኔን የጠላ አባቴንም ይጠላል፡፡ (ዮሐ.15:26) ነገር ግን ከአብ የሚወጣና እኔም ከአብ የምልከላችሁ የእውነት መንፈስ፣ አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሲመጣ፣ ስለኔ የመሰክራል፡፡ እናተም ከመጀመሪያ ጀምሮ ከኔ ጋራ አብራችሁ ስነበራችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡
    (ዮሐ.16፡1-3) ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይህንም የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ሰለማያውቁ ነው፡፡
    (ዮሐ.16:7-8) እኔ ግን እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ የኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፣ ምክንያቱም እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ (ጰራቅሊጦስ፣ መንፈስ ቅዱስ) ወደእናንተ አይመጣም፣ እኔ ከሄድሁ ግን ወደ እናንተ እልከዋለሁ፡፡ እርሱ በመጣ ጊዜ ስለ ኅጢአት፣ ስለፍርድና ስለጽድቅም ሰዎችን ያስረዳል፡፡
    (ዮሐ.16:12-15) ገና የምነግራችሁ ብዙ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ይከብዳችኋል፡፡ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ የመራችኋል፤ምክንያቱም እሱ የሚናገረወ የሰማውን እንጂ የራሱን አይደለምና ነው፡፡ እርሱ ወደ ፊት የሚሆኑትን ነገሮች ይነግችኋል፤ የኔ ከሆነው ወስዶ ስለሚነግራችሁ ፣ እኔን ያከብረኛል፡፡---፡፡
    (ዮሐ.16:28) ከአብ ዘንድ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፣ እንደ ገናም ይህን ዓለም ትቼ ወደ አብ እሄዳሁ፡፡----፡፡ (ዮሐ.16:30) አንተ ሁሉን እንደ ምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማትፈልግ አሁን ዐወቅን፣ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፡፡
    (ዮሐ.16:32፡-፤) ነገር ግን አብ ከኔ ጋራ ስለሆነ ብቻዬን አይደለሁም፡፡
    በጠቅላላ አባትና ልጅ መሆናቸውን ለማወቅ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ዐሥራ ሰባትን ያነቧል፡፡
    (ዮሐ.19፡7) አይሁድም እኛ ሕግ አለን፣ ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ስላደረገ በሕጋችን መሠረት ሞት ይገባዋል አሉ፡፡
    (ዮሐ.10፡30) እኔና አብ አንድ ነን፡፡ይቆየን የቀጥላል
    በተከታታይ በክፍል በክፍል የምናቀርብላችሁ ይኖራል ተከታተሉን
    ምንጭ ለምን አልሰለምሁም ገፅ 11-15
    Posted by ደቂቀ ናቡቴ at 5:15 AM

    ReplyDelete
  8. ርግጥ ነው፣ ሥጋ በመልበሱ፣ ሥጋ ለብሶ ዓለምን ለማዳን ከኃጢአት በቀረ ሰው የሠራውን ሁሉ ሠርቷል፣ እህል በልቷል፣ውሃ ጠጥቷል፣ ጥቂት በጥቂት አድርጓል፤ ተርቧል፣ ተጠምቷል፣ በሥጋው ሰው የሆነ አምላክ የማርያም ልጅነውና፡፡ አሁንም በሥጋው ሰው ስለሆነ፣ ተገፏል፣ ተስቅሏል፣ ሙቷል በመለከቱ ሥጋውን ይዞ ያላንዳች ረዳት መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ተነሥቷል፣ ተነሥቶም ወደ ሰማይ በክብር ዐርጎ በአባቱ ቀኝ በሥልጣን በክብር ተቀምጧል፡፡
    እርግጥ ከመለኮቱ ከመዋሐዱ በፊት ሥጋውን የፈጠረ በመንፈስ ቅዱስ ወልድ እንዲዋሐደው ያደረገ፣ ያመቻቸ እግዚአብሔር አብ በሦስትነቱ ነው፤ ስለዚህም አባቴም (በመለኮቱ) አምላኪየም በትስብእቱ ይለዋል፡፡ አባቱም ልጄ ይለዋል፣ መለኮቱን ሲያይ፡፡ ሐዋርያትም የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ እግዚአብሔር አብ እያሉ ያስተማሩ ስለዚህ ነው፡፡(ዮሐ.20፡17፤2ቆሮ.1፡3፤ኤፌ.1፡3፤ጴጥ.1፡3፤17) እሱም ራሱ እንደ መለኮት ሲያሰብ አባቴ እንደ ሰውነቱ ሲያሰብ አምላኪየ ሲል ኑሯል፡፡ አስተምሯል፡፡
    ይህ ሁሉ ምስክር እያለ ነው እንዲዳት ፣ ኢየሱስ አምላክ ወይም የአምላክ ልጅ አይደለም የሚሉት፡፡
    እስከዚህ የአብን አባትነትና የወልድን ልጅነት፣ የመንፈስ ቅዱስን እስትንፋስነት በሐዲስና በብሉይ ከገለጥን በቁርአን ደግሞ እንዴት እንደሆኑ እንይ፡፡

    ሥላሴ በቁርአን
    (ሱራህ 4፡171) እናንተ የመጽሐፍ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰነን አትለፉ፣ በአላህም ላይ ከእውነት ሌላ አትናገሩ የማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መልእክተኛና ቃሉም ነው፤ ከእሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡
    እኛስ ምን እንላለን? ቃለ እግዚአብሔር የእግዚአብሔር ቃል ከማለት በቀር፡፡ ለእነ ዲዳት የእግዚአብሔር ልጅ ስንል በወሲብ የወለደው ነው የምንል ይመስላችዋል፡፡ ከዚህ ላይ በቁርአኑ እንደተገለጠው በአንድበቱ የሚወጣ ቃሉ እንጂ ከማርያም በወሲብ የወለደው የሚል ጤነኛ ክርስቲያን የለም፡፡ ለምን? ቢሉ እግዚአብሔር አብ መለኮት መንፈስ እንጂ ሥጋዊ አይደለም፡፡ ሥጋ የለውምና፣ ትስብእትን የተጎናጸፈ ሰው አይደለም፣ ቀጥሎም እሱም ወደ ማርያም አንድ መንፈስ አምጥቷል አለ፤ ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ ፤ ትስብእትን የተጎናጸፈ ሰው አይደለምና፣ ቀጥሎም እሱም ወደ ማርያም አንድ መንፈስ አምጥቷል አለ፤ ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ፤በዚህም መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ በከርሠ ድንግል ማደሩን ይናገራል፡፡ (ሱራህ፡19፡34) የማርያም ልጅ ኢየሱስ በእሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃሉ ነው፡፡ ማስተዋል የለ፣ የነአሕመድ ነገር፣ እኛስ እውነተኛ ቃል እግዚአብሔር ነው እንላላን እንጂ ምን እንላለን? ከዚህ አስቀድሞም በሉቃስ ወንጌል (4፡18-20) የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ መልካም ዜናን ለድኆች እንዳበስር ሹሞኛል፤ ለታሰሩት መፈታተን፣ ለታወሩት ማየትን እንዳውጅና የተጨቁኑትንም ነጻ እንዳወጣ ልኮኛል፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ምዕራፍ ፡19፡30፡ ሕፃኑም አለ፤ እኔ የእግዚአብሔር ባርያ ነኝ(በሥጋው) መጽሐፍን ሰጥቶኛል፣ ነቢይም አድርጎኛል፡፡ በየትም ስፍራ ቢሆን ቡሩክ አድርጎኛል፡፡ ለእናቴም ታዛዥ አድረጎኛል፤ ትዕቢተኛና እምቢተኛም አላደረገኝም፡፡---፡፡በመንፈስ እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች በምን ይለያያሉ? ዓለምን ለማዳን በትሕትና የመጣው የወልደ እግዚአብሔር ቃላት ናቸው፡፡ ምስጢረ ሥላሴን ወስኖ አሰተምሮት የዐረገ ክርስቶስ ነው፡፡ እነ ዲዳት ግን በአራተኛው መቶ ዘመን በ325 በኒቅያ ነው የተወሰነው ይላሉ፤ ተሳስተዋል፣ ለምን ቢሉ? ከጰራቅሊጦስ አንሥቶ እስከ ዘመነ ቆስጠንጢኖስ ያለው ዘመን ለክርሲቲያን ዘመነ ሰማዕት፣ ዘመነ ስደት ይባላል፤ በዚህ ዘመን ክርስቲያኖች እንደልባቸው ለመገናኘትና ተገናኝተውም እንደልባቸው ለመናገር ስላልቻሉ፣ በቀላሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመነ ሁሉ ክርስቲያን ይባል ነበር፤ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ግን መጻሕፍት ተጠንተው፣ምስጢራት በቅዱሳት መጽሐፍት ተመርምረው ተወስስኑ፤ መናፍቃንም ተወገዙ፣ ኢምሁራንም ተማሩ፡፡
    ወስብሃት ለእግዚአብሄር
    ይቆየን የቀጥላል
    በተከታታይ በክፍል በክፍል የምናቀርብላችሁ ይኖራል ተከታተሉን
    ምንጭ ለምን አልሰለምሁም ገፅ 11-15
    Posted by ደቂቀ ናቡቴ at 5:15 AM

    ReplyDelete
  9. le muslimoch milash a bitsef.....ወልድ ተወለደ ስንል ምን ማለት ነው? መወለድ ማለት የወላጁን ባህርይ ይዙ የሚገኝ ማለት ነው። ለምሳሌ/ምሳሌ ትክክለኛውን እንደማይወክል ተረዱልኝ/ ከሰው የሚወለድ ሁሉ ሰው ነው። ከሰው የተወለደ ሁሉ የሰውነትን ባህርይ ይይዛል። ከወፍ የሚወለድም ሁሉ የወፍ ባህርይ ይይዛል። ለምሳሌ ወፍ ይበራል ማነኛውም ከሚበር ወፍ የሚወለድ ሁሉ አደጋ ካልገጠመው በስተቀር በራሪ ሆኖ ነው የሚፈጠረው።
    የወልድ መወለድም እንዲሁ ከአባቱ ባህርይን ነሳ እንላለን። ይህም ማለት አብ እግዚአብሔር እንደሆነ ወልድም እግዚአብሔርነትን ባህርይው ነው፤ አብ አምላክ እንደሆነ ሁሉ ወልድም አምላክ ነው። አብ ፈጣሪ እንደሆነ ሁሉ ወልድም ፈጣሪ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ ማርያም ከመገለጡ በፊት ነበረ ከአባቱም ጋር የተካከለ ባህርይ ነበረው።

    ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠ ነው፡

    መወለድን ከላይ እንደተመለከትነው ከወላጁ ባህርይን መውሰድ ነው መፈጠር ደግሞ በአንድ አካል መሰራት ማለት ነው። ለምሳሌ እግዚአብሔር ሰውን ፈጥሯል ሰው ግን አምላክ አይደለም፤ እግዚአብሐየር ምደርን ፈጥሯል ምድር ግን ጌታ አይደለችም። ሰው መኪና ፈጥሯል፤ መኪና ግን የሰውነት ባህርይ የለውም። ሰው አሻንጉሊት ፈጥሯል አሻንጉሊት ግን ሊሄድ አይችልም። ሰው ኮምፒዩተርን ፈጥሯል ኮምፕዩተር ግን ሰውን ሊተካ አይችልም።

    በአጠቃላይ ፍጡርና ፈጣሪው የተለያዩ ናቸው። ክርስቶስ ከአባቱ የተወደ ነው፡ የተፈጠረ አይደለም። በመሆኑም ከአባቱ ጋር አንዲት ስልጣንና ክብር አለው።.....http://wongelforall.wordpress.com/

    ReplyDelete
  10. le muslimoch milash bitsef መጽሐፍ ቅዱስ ስለኢየሱስ ነግሮ እንዲሁ አልተወንም። ይልቁንም ስልጣኑን ጭምር አስረግጦ ይናገራል እንጂ። ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለሆነ አምላክ ስለሆነ ጌታ ስለሆነ ፈጣሪ ስለሆነ የአምላክ ስልጣን ሁሉ ለእርሱ አለው። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ስልጣን እንዳለው ተመራምረን እንድንደርስበት ብቻ አልተወንም በሚገባ ልናውቃቸው የሚገቡ የኢየሱስ ስልጣኖችን ጠቅሶልናል።

    በመሆኑም ካለው አምላካዊ ስልጣን ውስጥ በቀላሉ የምንረዳቸውን የተወሰኑትን እንጠቅሳለን።
    1.ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጂ ነው፦ ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉስ አምላክ ጌታ ስለሆነ ፈራጂ ነው። በሐጥአን የሚፈርድባቸው ለጻድቃን የሚፈርድላቸው ፍርድን የሚሰጥ እርሱ ኢየሱስ ነው።
    2ኛ ጢሞ 4፡ 1 በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤ በህያዋንና በሙታን ላይ የሚፈርደው እርሱ ክርስቶስ ነው። ፍርድን የሚሰጥ እርሱ እግዚአብሔር የሆነ ክርስቶስ ነው። ከእርሱ ፍርድ ይወጣል እንጂ ልመና አይወጣም።

    2ኛጢሞ 4፤ 8 ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ጻድቅና ፈራጂ ነው። ፍርዱም በአንድና በሁለት ሰው የሚወሰን አይደለም በሁሉም ላይ የሚፈርደው እርሱ ነው። ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ያለው። መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ ይፈርድላቸዋልና።

    2ኛ ቆሮ 5፡ 10 መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና። መፅሐፍ ቅዱስ ፍርድ እንዳለ ይነግረናል። ይህን ፍርድ ደግሞ በእያንዳንዳችን ላይ የሚደረግ ነው። በእያንዳንዳችን የሚፈረደውን ፍርድ የሚፈርደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ታዲያ ኢየሱስ ሲፈርድ መጀመሪያ ለምኖ ይሆን የሚፈርደው ? አይደለም ኢየሱስ የሚፈርደው በስራችን መጠን ነው። እርሱ እኛነታችንን ያውቃል በስራችን መጠንም ይፈርዳል።

    ራዕ 22፤ 12፡ እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ :: ክርስቶስ ስራችንን ስለሚያውቅ እንደስራችን መጠን እንደ ሃይማኖታችን መጠን ፍርድን ይሰጣል። ፍርድን ሲሰጥ ሰዎች አማልደን ይሉት ይሆንን ? አይባልም እርሱ ፈራጅ እንጂ አማላጂ አይደለምና።
    እንዲያውም ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተናገረው ፍርድን የሚያደርገው እርሱ ኢየሱስ እንጂ አብ አይደለም። ይህ ሲባል የአብና የወልድ ፈቃድ የተበለያየ ነው ማለት አይደለም የአብም ሆነ የወልድ ፈቃድ አንድ ነው ሆኖም ፍርዱን የሚሰጠው የሚፈርደው እርሱ ኢየሱስ ነው። አብ በማንም አይፈርድም ፍርድ የእርሱ የወልድ ስልጣን ነው።
    ዮሐ 5-22-23 ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም :: ፈራጂ ወልድ ከሆነ እንግዲህ ወልድ የሌለው ስልጣን አለ ልንል እንችላለን ? የለም ወልድ ራሱ ነው የሚፈርደው የሚጸድቁትንም ሆነ ወደ ኮነኔ የሚሄዱትን የሚለይ የሚፈርድ እንደ ስራቸው የሚያስረክብ እርሱ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው from http://wongelforall.wordpress.com/ orthodoxawi blog new

    ReplyDelete
  11. ene gar abreh mesrat siletyekegh new ene gena ye univercity sostegha amet ye hikmna temari mehonen tsfelh neber yihen degmo from ......http://wongelforall.wordpress.com/........ ageghuna abrachihu mesrat kechalachihu endtanebew gabezkuh አዲስ መጽሐፋዊ ጽሑፍ
    July 16, 2010
    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

    ከዚህ ቀጥሎ በተከታታይ በመጽሐፍ መልክ እየተዘጋጀ ጽሑፍ በድህረ ገጻችን ይቀርባል። የመጽሐፉ አላማ ከዚህ በታች በመግቢያው ላይ እንደተገለጠው ሲሆን ኦርቶዶክስ ክርስትና ትምህርት ላይ የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎችን በማንሳት ለማወያየትና ክፉውን ከመጥፎው እንድለይ እንዲረዳን ታስቦ በመዘጋጀት ላይ ያለ ነው። ማስተካከያ ወይም አስተያየት ካለዎት እንዲጽፉልን የተለመድ ጥያቄያችንን እናቀርባለን።

    በክርስትና ላይ ግር ያለዎትን ወይም ጥያቄ የሆነብዎትን ይላኩልን የክርስቶስ ቃል ወንጌል መልስ አለው። ጥያቄዎን ማወቃችን መጽሐፍትን ለማገላበጥ ይጠቅመናል። ለሌሎች ወንድሞችም መልስ እንዲያገኙ እየረዱ ነው። ማነኛውም ሰው ለድህረ ገጹ ይመጥናሉ ይሆናሉ የሚላቸውን ክርስቲያናዊ ትምህርቶችንና ጽሑፎች በአድራሻየ ቢልክልኝ እያየሁ የማወጣ መሆኔን ለመግለጽ እወዳለሁ። ...... በመጽሐፍ መሳተፍ ለምትፈልጉም ድህረ ገጻችን ክፍት ነው። በአድራሻችን ላኩ። yilal

    ReplyDelete
  12. “አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ ዘእንበለ ዳዕሙ በትስብእቱ” የሚለውን ቃል አላነበበም ልበል!!!!

    ReplyDelete

FeedBurner FeedCount