Saturday, April 5, 2014

ገብር ኄር ዘቀዳሚት ሰንበት

በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 27 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 በሦስትነት አንድ፣ በአንድነት ሦስት በሚሆን፣ በባሕርይ አንድ በሚሆን፣ በመለኮትም በሚተካከል በእግዚአብሔር ስም፣ በአንዲት ፈቃድ በሚተባበሩ በምሥጋና መብረቅ በተጋረዱ፣ በሚነድ እሳትም በሚሸፈኑ ጥንትና ፍጻሜ በሌለው በአንድ አምላክ ሰላም ይሁንላችሁ::


 እንደሌሎቹ ሳምንታት ሁሉ የዛሬ የቀዳሚት ሰንበት የጾመ ድጔ ገብር ኄር ድርሰቱ ከሌሎቹ ቀናት አጠር ያለች ናት:: እነሆ እኛ የተመረጡ ጥቂት ቃላትን በዜመኛው ቋንቋ በመላእክት ምሥጋና እያዜምን እንቆያለን:: የቀደመች ሰንበት ናትናናክብር ሰንበቶ” ብሎ ይጀምራል ፡፡ “ናክብር ሰንበቶ በተፋቅሮ ወኢንኅድግ ሥርዓቶ ወናልዕል ስሞበመፋቀር ሰንበቱን እናክብር፤ ሥርዓቱንም አንተው፡፡ በአንድነትም የእግዚአብሔር ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ፤ በመስቀሉ ገነትን የከፈተውን ክርስቶስን እናመስግነው::” እንደ ትላንትናው ባለ ምሥጋና መስቀል በሉ፤ መስቀሉን ተመርኮዙ፤ ክርስቶስ ይጠብቃችሁ፤ ሁሉን ፈጽሞ ባረፈባት ቀን የምሥጋና አባት ከእናንተ ጋር ይሁን::

 ወነገረ መስቀሉሰ ዕፁብ ለተናግሮየመስቀሉ ነገርስ ለመናገር ድንቅ ነው፤ መስቀል ለአሕዛብ መመኪያ (ሐብት) ለነገሥታት ክብርና ውበት ነው::” አብ ሰንበትን ቀደሳት፤ ወልድ ደግሞ ከፍ ከፍ አደረጋት:: በመስቀል የተሰቀለው ክርስቶስ ወደ ምኩራብ ገብቶ ሰንበትን ያከብሯት ዘንድ አስተማራቸው:: ይህች ቀን ከሌሎች ሁሉ ትከብራለች ለጽድቅ ተሰርታለችና ሁሉ ከኃጢአት ድካም ከዚህ ዓለም ሃሳብ ያርፍባት ዘንድ ተፈጥራለች:: እንግዲህ ሕዝበ ክርስቲያኖች ይላል ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሰው እንግዲህ በመስቀሉ ከእስር ፈትቶ በዚህች ቀን ሰላምን እንኖር ዘንድ ከኃጢአት ቀንበር ነፃ አደረገን:: ስለዚህ በሁሉ በዚህች ቀን እረፉ፤ ስደታችሁ አይሁን፤ መገዛታችሁ አይሁን፤ ድካማችሁ አይሁን፤ በዚህች ቀን ደስ ይበላችሁ:: ዛሬ የማይደሰተው የሚሰደደው አጋንንት ብቻ ነው::

 ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘበመስቀሉ ተሠዱ አጋንንት ለዘቀደሰ ለሰንበትበሰማይ ለእግዚአብሔር ምሥጋና በምድርም ሰላም በመስቀሉ አጋንንት ተሰደዱ ሰንበትን ቀደሳት::” ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን::

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount