Tuesday, April 28, 2015

የጉባኤ ጥሪ ከዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት

“ተዋሕዶ ሃይማኖታችን፣ ቤተ ክርስቲያን እናታችን” በማለታቸው በዓለማቀፉ አሸባሪ ቡድን በአይሲስ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታትን ለማሰብ የመንበረ መንግሥት (ግቢ) ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ሚያዝያ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤ አዘጋጅቷል፡፡ በዕለቱ “ሰማዕትነት በዘመናችን” በሚል ዐቢይ ርእስ የምክክር ጉባኤ የሚደረግ ሲኾን ሚያዝያ 20፣ 21፣ እና 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ዠምሮ የጸሎት መርሐ ግብር ይካሔዳል፡፡

በዕለቱ፡-
·        ጸሎት በገዳማችን ካህናት፤
·        መዝሙር በሰንበት ትምህርት ቤቱ መዘምራን፤
·        ትምህርት በተጋባዥ መምህራን፤
·        ሥነ ጥበባዊና ሌሎች ዝግጅቶች የሚቀርብ ሲኾን
ርሶም የተዋሕዶ ሃይማኖታቸውን በአደባባይ ለዓለም የመሰከሩ ወንድሞቻችን ሰማዕታትን ለማዘከር በተዘጋጀው በዚኽ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡
·        ሰዓቱ፡- ከቀኑ 9፡00-12፡00 ሰዓት
·        ቦታ፡- በዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
. ቀን፦ ሚያዝያ 23 ቀን 2007 ዓ.ም.

“ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡፡  

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount