Showing posts with label የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት. Show all posts
Showing posts with label የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት. Show all posts

Tuesday, October 30, 2012

ጌታ ሆይ አምናለሁ -የዮሐንስ ወንጌል የ40ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.9)


       በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  በምዕራፍ 8 እንደተመለከትን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚነግራቸውን ነገር ከማመን ይልቅ አይሁድ “ጋኔን አለብህ” /8፡48/ ብለው በድንጋይ ሊወግሩት ሽተው ነበርና አንድም “አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ” /8፡58/ ብሏቸው ነበርና ቁጣቸውን አብርዶ ቀዳማዊነቱን በገቢር (በሥራ) ያስረዳቸው ዘንድ ወደደ /መዝ.51፡4/፡፡ ስለዚህም ሲያልፍ ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው (ሲለምን) አየ /ቁ.1/። ይህ ዐይነ ሰውር ሰው የዓይን ምልክት እንኳን አልነበረውም፡፡ እንዲሁ ልሙጥ ግንባር ነበረው እንጂ፡፡ ስለዚህ ሰውዬው ሳይሆን ክርስቶስ አየው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ክርስቶስ ዕዉሩን በልዩ እይታ (በፍቅርና በሐዘኔታ) እንዳየው አስተዋሉ፤ ደነቃቸውም፡፡ አስቀድሞ መጻጉዑን ሲፈውሰው፡- “ዳግመኛ እንዳትበድል” ብሎት ስለነበረ /5፡14/ “ይህ ዕዉር ሆኖ የተወለደውም ዕዉርነቱ ከበደል የተነሣ ነው ማለት ነው” ብለው አሰቡ፡፡ አሳባቸው ግን ግራ አጋባቸው፡፡ ስለዚህም፡-  መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ነው ወይስ ወላጆቹ?” ብለው ጌታን ጠየቁት /ቁ.2/። ጌታችንም፡-እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው በራሱ ኃጢአት ይቀጣል እንጂ አባት ስለ ልጅ ልጅም ስለ አባት አይቀጣምና /ዘዳ.24፡16/፡፡ ታድያ እርሱ ነውን? ብትሉም አይደለም እላችኋለሁ፡፡ እንግዲያ ስለምን ዓይነ ስውር ሆነ? ብትሉም የእግዚአብሔር ሥራ (አስቀድሞ አዳምን ከምድር አፈር የፈጠርኩት ቀዳማዊ የምሆን እኔ መሆኔን) በእርሱ እንዲገለጥ ነው እላችኋለሁ /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Tatation’s Diatessaron, 28 /፡፡

Tuesday, October 16, 2012

አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ- የዮሐንስ ወንጌል የ 39ኛ ሳምንት ጥናት


(ዮሐ.8፡48-59)

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ክፋትን የሚሠራት ሰው በጣም የባሰና አሳፋሪ የሚያደርገው ተሸማቅቆና አፍሮ ራሱን መደበቅ ሲገባው ይባስኑ ለስሕተቱና ለክፋቱ ምክንያትን እየፈለገ ሲቀጥልበት ነው፡፡ አይሁዳውያንም እንዲህ ዓይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እናንተ የአብርሃም ልጆች አይደላችሁም፡፡ የአብርሃምስ ልጆች ብትሆኑ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር፤ ከአብ ዘንድ በሕልውና ያየሁትንና የሰማሁትን እውነቱን የምነግራችሁ እኔን ልትገድሉኝ ትሻላችሁና፡፡ አብርሃም እንዲህ አላደረገም፤ ነፍስ አልገደልም፡፡ መግደልስ ይቅርና ልጁን ነበር ለእግዚአብሔር የሠዋው፡፡ ነፍስስ መግደል ይቅርና የወጣው የወረደውን፣ ያለፈው ያገደመውን እንግዳ ነበር ሲቀበል የነበረው፡፡ እንኳንስ እንዲህ ያለ ትምህርት አግኝቶ ነግረውትና አስተምረውት አላምንም ማለት ይቅርና ወጥቶ ወርዶ ነበር ፈጣሪውን ያገኘው፡፡ ስለዚህ እናንተ ልትገድሉኝ እንደምትሹ አባታችን የምትሉት አብርሃም እንዲህ አላደረገም፡፡ በዚያም ላይ ደግሞ ባስተምራችሁ አልተቀበላችሁኝም፡፡ ስለዚህ የአባታችሁኝ የሰይጣን ሥራን ትሠራላችሁና አባታችሁ አብርሃም አይደለም፡፡ እናንተስ ከእግዚአብሔር አይደላችሁም” ብሎ ማየት ያቃታቸውን የመረቀዘ ቁስላቸውን ቢያሳያቸው የባሰ ተናደዱ (ይህን የበለጠ ለማንበብ እዚህይጫኑ)፡፡ በቁስላቸው ላይ ጨው ጨመሩበት፤ “አንተ በእውነት ሳምራዊ ነህ (አይሁዊ አይደለህም) የምንልህ ስለዚሁ አይደለምን? ጋኔን አድሮብሃል፤ የእግዚአብሔር ልጅ አይደለህም የምንልህስ በዚህ ምክንያት አይደለምን?” ብለው ከወገንነት አውጥተው ከይሁዲነት አግልለው ሰደቡት /ቁ.48/፡፡ እንደ እነርሱ አስተሳሰብ ሳምራዊ ማለት የተናቀ፣ የሚለውን የማያውቅና እንዲሁ የሚዘባርቅ፣ ከአይሁድ ጋር የማይተባበር ይልቁንም የአይሁድን እምነት የሚያናንቅ ነው፡፡ በዚህ አነጋገራቸው ጌታችን ጸረ አይሁድ አቋም እንዳለው አስመስለው ለማቅረብም ሞክረዋል፡፡ አይሁድ ሆይ! ጋኔን ያደረበት ማን ነው? እግዚአብሔርን የሚያከብር ወይስ እግዚአብሔር አብን ያከበረው ወልድን የሚሳደብ? /St. John Chrysostom, Homily 55/፡፡


Wednesday, October 3, 2012

በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀመዛሙርቴ ናችሁ


    የዮሐንስ ወንጌል የ38ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.8፡21-47)
  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
 (ከቻሉ ጸልየው ይጀምሩ)
  ልበ ስሑታን የሆኑ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ጌታችንን ለመግደል፣ ከሕዝቡ ልብ ለማውጣት ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልፈለጉበት ስሕተት የለም፡፡ ሆኖም ንጹሐ ባሕርይ ነውና ይህን ያገኙበት ዘንድ አልተቻላቸውም፡፡ እግዚአብሔር ነውና በልባቸው የሚያመላልሱትን ስለሚያውቅ ኃጢአታቸውን አውቀው ፍቅሩን እንዲረዱለት፤ የታመሙትን (እነርሱን) ፍለጋ እንደመጣ እንዲያውቁለት በጥበብ፣ በኃይል እንዲሁም በሥልጣን ይነግራቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሚያስፈራሩ ቃላት ሌላ ጊዜም በሚጋብዙ የትሕትና ቃለት ያምኑበት ዘንድ ይጠራቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን ይህን እንዳያውቁ በምርጫቸው ልባቸውን አደንድነውታልና ይገድሉት ዘንድ ፈለጉ፡፡

Sunday, September 16, 2012

እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ


  የዮሐንስ ወንጌል 37 ሳምንት ጥናት (ዮሐ.812-20)

     በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

  በምንዝር በያዝዋት ሴት ላይ ለመፍረድ ተሰብስበው የነበሩት አይሁድ ፈሪሳውያን ጌታችን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ሆይ! ኃጢአታችሁ ከዚህች ሴት ኃጢአት የባሰ እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ ታውቁት ትረዱት ዘንድም አሁን ሕሊናችሁን መርምሩ፡፡ ስለዚህ እናንተው ራሳችሁ ወንጀለኞች ሳላችሁ በዚህች ሴት ላይ የምትፈርዱ አትሁኑ፡፡ ይልቁንም እርሷን ከመውቀሳችሁና ከመክሰሳችሁ በፊት ራሳችሁን የምትወቅሱ ሁኑ፡፡ እርሷ ተወግራ እንድትገደል የምትፈርዱ ከሆነ ግን እናንተም ከዚያ ነጻ አይደላችሁምብሏቸው እነርሱም ይህን ዘለፋ በሰሙ ጊዜ ሕሊናቸው ወቅሷቸው በፊት ከገቡት ጀምሮ በኋላ እስከ ገቡት ድረስ አንድ አንድ እያሉ እየወጡ ሄደው ነበር /.9/፡፡(በዚህ እስ ላይ ይህን ይመልከቱ እኔም አልፈርድብሽም- የዮሐንስ ወንጌል የ36ኛ ሳምንት ጥናት(8፡1-11)

  ሆኖም ግን ተመልሰው መጡ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ቂመኛ አይደለምና ዳግመኛ አስተማራቸው፡፡ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው /ቁ.12/፡፡ እንዴት ያለ ፍቅር ነው? እንደምን ያለ መውደድ ነው? ፍቁራን ሆይ! የጌታን ንግግር ታስተውሉታላችሁን? እንዲህ ማለቱ ነበር፡-“ፈሪሳውያን ሆይ! እናንተ በመጻሕፍተ ኦሪት የዘለዓለም ሕይወት እንዳለችሁ ይመስላችኋል፤ እነርሱንም ትመረምራላችሁ፡፡ እነርሱ ግን ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው /ዮሐ.5፡39/፡፡ እንግዲያውስ ወደ እኔ ኑ እንጂ በዚያ የምትቀሩ አትሁኑ! ዳዊት ‘የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን’ እንዳለ /መዝ.36፡6/ የሕይወት ምንጭ እኔ ነኝና ወደ እኔ ቅረቡ እንጂ በጨለማ የምትቆዩ አትሁኑ፡፡ እውነተኛው ብርሃን እኔ ነኝና ወደ ብርሃን (ወደ እኔ) ኑ! በጨለማ ላለ ሰው ብርሃን ያስፈልጓል፡፡ የተጠማ ሰውም የሚያረካ መጠጥ ያስፈልጓል፡፡ እንግዲያውስ የእነዚህ ምንጫቸው እኔ ነኝና ታገኝዋቸው ዘንድ ወደ እኔ ቅረቡ (በእኔ እመኑ)፡፡ ከእናንተ መካከል አንዱ በሌሊት ውኃ ቢጠማው ተነሥቶ ኩራዝን የማያበራ ማን ነው? ኩራዙንም ተጠቅሞ ውኃ ቀድቶ የሚጠጣ አይደለምን? እንግዲያውስ እናንተም በብርሃኔ ብርሃን የሆንኩትን እኔን ያዙና ዳግመኛ ጽምዓ ነፍሰን የማያስጠማ የሕይወትን ውኃ ጠጡ፡፡ ልጆቼ ሆይ! በጨለማ (በድንቁርና) መኖርን ስለምን ትመርጣላችሁ? እናንተን እንዲሁ አፍቅሬ አማናዊው ብርሃን የምሆን እኔ ወደ እናንተ ስመጣ ስለምን ዐይነ ልቡናችሁን በመዝጋት እኔን ከማየት ትከለከላላችሁ? አባቶቻችሁ ከምድረ ግብጽ ለመውጣት ፊት ለፊት የሚመራቸውን ዓምደ ብርሃንን ተከትለው ከባርነት የወጡ አይደሉምን? /ዘጸ.13፡21/ እንግዲያውስ እናንተም ወደ እውነተኛው ሀገራችሁ (ወደ ገነት መንግሥተ ሰማያት) ለመግባት ብርሃን እኔን ተከተሉ፡፡ እኔ የፍልስጥኤም ወይም የገሊላ ወይም ደግሞ የይሁዳ ብቻ ሳልሆን የዓለም ሁሉ ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ(የሚያምንብኝ) ቢኖር የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል፡፡ ክብርን፣ ዕውቀትን፣ መንግሥተ ሰማያትን ያገኛል እንጂ በሐሳር፣ በጨለማ ፣ በገሃነም አይመላለስም፡፡ የሚከተለኝ ቢኖር በሴሰኛይቱ ሴት እንዳደረጋችሁት ሳይሆን በራሱ ኃጢአት ላይ ስለሚፈርድ በእኔ አምኖ ይኖራል፡፡ ወደ ክሕደት፣ ወደ ገሃነም፣ በሌሎች ላይ ወደ መፍረድ፣ ወደ ክፉ ነገር አይሄድም፡፡ የሕይወትን ውኃ ክብረ መንግሥተ ሰማያትን ታገኛል፡፡ ስለዚህ በእኔ እመኑና ከስሕተት ከክሕደት ውጡ” /St. Cyril of Alexandria on the Gospel of John, 5:2/፡፡ 

   ፈሪሳውያን ግን ይህን ፍቅር ከመረዳት ራቁ፡፡ መድኅን የሆነው ስሙ ከፍ ከፍ ይበልና አፍቃሪያቸውን እንደ “ዕሩቅ ብእሲ” አይተዉት “የሌለውን አምላክነት” ለራሱ የወሰደ መሰላቸው፡፡ ስለዚህ፡- “አንተ ስለ ራስህ ትመሰክራለህን?” ራስህን የምታመሰግን፣ ራስህንም የምታደንቅ ከሆነማ… አሉት፡፡ ሐሰት የባሕርይው ያይደለ አምላክ “ምስክርነትህ (የምትናገረው ሁሉ) እውነት አይደለም” አሉት /ቁ.13/።  የሚደንቀው ግን

Monday, September 3, 2012

እኔም አልፈርድብሽም- የዮሐንስ ወንጌል የ36ኛ ሳምንት ጥናት(8፡1-11)


 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
  ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይሁድ ከሚያከብሩት የዳስ በዓል በኋለኛው ቀን “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፡፡ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወትን ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል” ብሎ አሰምቶ ከነገራቸው በኋላ፣ አለቆቹና ካህናትም ክርክራቸውን ከፈጸሙ በኋላ /7፡53/ “ወደ ደብረ ዘይት ሄደ” /ቁ.1/። ካስተማርን፣ ከገሰጽን፣ ከመከርን በኋላ የራሳችን የሆነ የጽሞናና የጸሎት ጊዜ ሊኖረን እንደሚገባ ሲያስተምረን አንድም ማደርያው በዚያ ነበርና ወደ ደብረ ዘይት ሄደ /St. John Chrysostom/፡፡

  ከዚያ ሲጸልይ አድሮም እንደ ልማዱ ገስግሶ ወደ መቅደስ ሄደ /ቁ.2/፡፡  የመልካም አገልጋይ ባሕርይ እንዲህ ነው፡፡ መልካም አገልጋይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል አገልግሎቱን በፍቅር ይፈጽማል፡፡ ስለዚህ ጌታ የሚወዳቸውን ልጆቹ ያገኝ ዘንድ ወደ ምኵራብ ገባ፡፡ “ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ”፡፡ ወንጌላዊው ሉቃስ “ሕዝቡም ሁሉ ይሰሙት ዘንድ ማልደው በመቅደስ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር” እንዲል ትምህርቱን ያስተምራቸው ጀመር /ሉቃ.21፡38/፡፡

   በዚህ ጊዜ ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ሕዝቡ የጌታን ትምህርት ያደምጡ ዘንድ እንዴት በጧቱ እንደተሰበሰቡ አዩ፡፡ ውስጣቸውም በቅንአት ተቃጠለና ትምህርቱን ያደናቅፉ ዘንድ ስትሴስን ያገኟትን አንዲት ሴት አስረው ይዘዋት መጡ፡፡ አምጥተውም ጌታ ካለበት ጉባኤ መካከል አቆሟት /ቁ.3/፡፡ ከዚያም “መምህር ሆይ!” ይሉታል /ቁ.4/፡፡ መምህርነቱን አምነውበት አልነበረም /7፡47/፡፡ አመጣጣቸው ለተንኰል ስለ ነበር እንጂ፡፡ ስለዚህ “ይህች ሴት ስታመነዝር ስትሴስን ተገኝታ ተያዘች (አግኝተን ያዝናት)፡፡ ሙሴም እንደዚህ ያሉት (አንድ ወንድ ለአንድ ሴት፤ አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ይሁን የሚለውን ሕግ ተላልፈው ቢገኙ) እንዲወገሩ አዘዘን፤ አንተስ ምን ትላለህ (ምን ትፈርዳለህ)?” አሉት /ቁ.5/፡፡  እንደነርሱ ሐሳብ ይህች ሴት ስትሴስን ስለ ተገኘች በዚህ ምድር በሕይወት መኖር “የማይገባት” ሴት ነች፡፡ የሚደንቀው ግን ይዘዋት የመጡት ወደ ይቅርታ አባቷ ወደ እግዚአብሔር መሆኑን አለማወቃቸው ነው፡፡ ይዘዋት የመጡት በዓለም ላይ እንዲፈርድ ሳይሆን ዓለምን እንዲያድን ወደ መጣው ጌታዋ

Friday, August 24, 2012

ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ- የዮሐንስ ወንጌል የ35ኛ ሳምንት ጥናት (ዮሐ.7፡37-ፍጻሜ)!


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

  በ33ኛ ሳምንት ጥናታችን እንደተናገርን አይሁድ የዳስ በዓልን የሚያከብሩት ሰባት ቀን ሙሉ እንደ አንድ ቀን ነው /ዘሌ.23፡34/፡፡ በበዓሉ እኩሌታ ማለትም በአራተኛው ቀንም ጌታ በሕቡዕ ያይደለ በይፋ በስዉር ያይደለ በግልጥ ማስተማሩን መገሰጹን ተመልክተናል፡፡ አሁን ደግሞ በበዓሉ በኋለኛው ቀን፣ የደስታ ቀን ብለው በሚያከብሩበት በመካተቻው፣ በመጨረሻው፣ በመሰባበቻው ቀን እንዲህ ብሎ አሰምቶ ተናገረ፡- ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል” /ቁ.37-38/። እንዲህ ማለቱ ነበር፡- ማንም ጽድቅን የተጠማ ቢኖር፣ ማንም ሕይወትን የናፈቀው ቢኖር፣ ማንም መንግሥተ ሰማያትን መውረስ የሚፈልግ ቢኖር፣ ማንም እኔ የምሰጠውን የጽድቅ ውኃ መጠጣት የሚሻ ቢኖር፣ ማንም እኔ የምሰጠውን ሀብታተ ምሥጢራትን ጸጋውን መቀበል የሚፈልግ ቢኖር… ወደ እኔ ይምጣ፤ በእግረ ሥጋ ሳይሆን በእግረ እምነት ወደ እኔ ይቅረብ፤ በእግረ በቀል ሳይሆን በእግረ ፍቅር ወደ እኔ ይጠጋ፤ ቀርቦም የምሰጠውን ውኃ ይጠጣ፤ መጥቶም ከዙፋኔ የሚወጣውን እንደ ብርሌም ሚያንጸባርቀው የሕይወትም ውኃ ከሚሆን ወንዝ ይጠጣ ይቀበል /Augustine, On the Gospel of St. John, tractate 32:2./፡ ሙሴ ከሰጠው ጊዜአዊ ጥምንም ከሚያረካው ውኃ ተላቆ ይምጣና አማናዊውን የሕይወት ውኃ ምንጭ ዐለት በውስጡ ያኑር፡፡ ይህን እንዴት ማግኘት እችላለሁ ብሎ የሚቸገርም ከቶ አይኑር፡፡ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው የተናገሩለት፣ ሱባዔ የቆጠሩለት መሲሕ ክርስቶስ እርሱ ነው ብሎ በእኔ ይመንና መጽሐፍ እንደተናገረ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል (በእርሱ ምክንያት ቃሌ ሲነገር ልጅነት ሲሰጥ ብዙዎች ሲያምኑበት ይኖራል)፤ በፈሳሾች አጠገብ እንደሚበቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች ይሆናል /ኢሳ.44፡3/፤ ከተድላ ፈሳሽ ይጠጣል /መዝ.36፡8/፤ የሕያዋን ምንጭ የሚሆን መንፈስ ቅዱስ ያድርበታል /ኤር.2፡13/፤ የእግዚአብሔርን ቸርነት ይቀምሳል ያያልም /መዝ.34፡8/፤ በኢዩኤል ነብይ የተነገረው ትንቢት በእርሱ ላይ ይፈጸማል” /ኢዩ.2፡28-32፣ Saint Cyril the Great, Commentary on the Gospel of John, Book 5/፡፡

 ይህም አስቀድመን እንደተናገርን ያመኑበት ሰዎች ሊቀበሉት ስላላቸው ሀብታተ መንፈስ ቅዱስ የተናገረው ነው፡፡ ይህን ያለው ምእመናን በመንፈስ ቅዱስ ስለሚያገኙት ምሥጢር፣ በመንፈስ ቅዱስ ስለሚገኙት ልጅነት ሲገልጽ ነው፡፡ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ (ያስተውሉ! ከዚያ በፊት ክብሩ በሰው ዘንድ አልታወቀም አልተገለጠም ነበር ለማለት እንጂ ሎቱ ስብሐትና ክብር አልነበረውም ማለት አይደለም፡፡ በብዙዎች ዘንድ ጌታ መሆኑ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የታወቀው ከስቅለቱ በኋላ ከትንሣኤም በኋላ ስለ ሆነ ነው) ስላልተሰቀለ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና /ቁ.39/። ይህ ማለት ግን መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስ ከመሰቀሉ በፊት በሰው ልጆች ላይ አልነበረም ማለት አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በነቢያት ነበረ፤ መጽሐፍ እንደተናገረ አስቀድሞ በእመቤታችን ላይ ወርዷል፤ ወንጌል እንደመሰከረ መንፈስ በስምዖን አረጋዊ ላይ ነበረ፤ በነቢይቱ ሀና ላይ ነበረ፡፡ ስለዚህ አሁን እየነገረን ያለው አጠቃላይ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከበዓለ ኃምሳ በኋላ ሊሆን ስላለው ሁኔታ ነው /Augustine, tactate 32:7. /፡፡

  ከሕዝቡ አያሌ ሰዎች ይህን ቃል ሲሰሙ፣ “ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ” የሚል የጌታችን የፍቅር ግብዣ ሲያደምጡ በአራት ምድብ ተከፋፈሉ፡፡ በአንደኛው ምድብ የነበሩት ይህ በእውነት ሙሴ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል ብሎ የተናገረለት ነቢዩ ነው” አሉ /ዘዳ.15፡18/፤ ሁለተኛው ምድብ የነበሩት፡-ነቢዩ አይደለም ይህ ክርስቶስ ነው” አሉ፤ በሦስተኛው ምድብ የነበሩትና አወቅን ጠነቀቅን ያሉት ደግሞ፡-ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን? ክርስቶስ ከዳዊት ዘር ዳዊትም ከነበረባት መንደር ከቤተ ልሔም እንዲመጣ መጽሐፍ አላለምን?”  በማለት ጌታ በናዝሬት ገሊላ ማደጉ ናዝሬት ገሊላ የተወለደ ስለመሰላቸው ተደናገሩ /መዝ.132፡11፣ ሚክ.5፡2/። አራተኛው ምድብ ደግሞ ከጸሐፍትና ከፈሪሳውያን ከአለቆቹ ጋር ያበሩና ጌታን ለመግደል የሚያስቡ ሎሌዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሎሌዎች ክርስቶስን ለመያዝ ወደው ነበር ይዘውም ለአለቆቻቸው አሳልፈው ይሰጡት ዘንድ ሽተው ነበር፡፡ ሆኖም ግን በቃሉ ተማርከው አምነውበታልና አንድም ጊዜው አልደረሰምና ይህን ማድረግ አልተቻላቸውም /ቁ.40-44፣ Saint Cyril the Great, Ibid/፡፡

 አስቀድመን እንደተናገርን የመጨረሻው ቀን ማለት አይሁድ በደስታ የሚያከብሩት ቀን ነው፡፡ ዛሬ ግን ጸሐፍትና ፈሪሳውያን የደስታ ቀን ሊሆንላቸው አልቻለም፡፡ የደስታ ምንጭ የሆነውን ክርስቶስን ሊገድሉበት ፈለጉ እንጂ እርሱን ተቀብለው ደስታቸውን ፍጹም ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡ ውስጣቸው በቅንአት ተጠፍሯልና ይህን የክርስቶስ ፍቅር ማየት አልተቻላቸውም፡፡ የደስታ ቀን በሆነው ዕለት መንፈሳዊ ተግባራቸውን ትተው ሊገድሉት የሚፈልጉትን ክርስቶስ ይጠባበቁ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እንዳሰቡት አልሆነላቸውም፡፡

  ሎሌዎቻቸው (አራተኛው ምድብ ያልናቸው ናቸው!) ክርስቶስን ሳይዙ በመጡ ጊዜ፣ አስረን እናመጣዋለን ብለው ሄደው አምነው እየተደነቁ በመጡ ጊዜ፡-ለምድነው ያላመጣችሁት?” ብለው ተቈጡዋቸው። ሎሌዎቹ ግን አሳማኝ ምክንያት ነበራቸው፡፡ አለቆቻቸው ባይቀበልዋቸውም እንዲህ ሲሉ ሳይፈሩ አስረድዋቸው፡-አለቆቻችን ሆይ! ይህን ሰው ለምን ይዛችሁት አልመጣችሁም ብላችሁ የምቆጡን አትሁኑ፤ ይህ ሰው እንደተናገረው በዓለም ታይቶም ተሰምቶም ከቶ ከቶ አይታወቅም፡፡ እኛ መጻሕፍትን እናውቃለን ብለን እናስብ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ገና አላዋቂዎች መሆናችንን ዛሬ አይተን ተረድተን መጣን፡፡ እርሱ የሚናገረው ነገር ፍጹም መለኰታዊ ቃል ነውና፡፡ ይህ ሰው የሚናገረው ማንም ምድራዊ መምህር ሊያስተምረው ሊናገረው የሚቻለውም አይደለምና፡፡ ስለዚህ ይህን ሰው ፈጽመን ልንገድለው አይገባንም፡፡ በአፉ ተንኰል አላገኘንበትምና እንደ ሕጋችን ንጹሕ ሰው ልንገድል አይገባንም፡፡ እንደውም በሰቂለ ሕሊና ስናስተውለው ስናደምጠው እንደ እግዚአብሔር በኃይልና በሥልጣን ይናገራል እንጂ እንደ ዕሩቅ ብእሲ አይናገርም፡፡ ምክንያቱም ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ ያለ ነቢይ ሰምተንም አይተንም አናውቅምና፡፡ ታላቁ አባታችን ሙሴ እንኳን አንድ ቀንም ቢሆን በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ሲል አልሰማነውምና፡፡ ይህ ሰው ግን ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ፤ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል እያለ በሥልጣን ይናገራል፡፡ የሚናገረው ሁሉ ዕሩቅ ብእሲ የሚናገረው አይደለም” ብለው መለሱላቸው /ቁ.45-46፣St. Cyril the Great, Ibid/። ተወዳጆች ሆይ! የክርስቶስን ፍቅር የምታስተውሉ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም እነዚህን አለቆች እጅግ ከማፍቀሩ የተነሣ እንዲጠፉበትም ካለመፈለጉ የተነሣ ይመለሱለት ዘንድ ልባቸው ደንዳና ሆነ እንጂ ሊያደምጥዋቸው በሚችሉ ሰዎች ሲያስረዳቸው ነበርና፡፡

  ስለዚህ አለቆቹ ጭራሽ እንዲገባቸው አልፈቀዱምና ባሰባቸው፡፡ ሎሌዎቻቸውንም፡-እናንተ ደግሞ እንደነዚያ ሐዋርያት ሳታችሁን?” አልዋቸው /ቁ.47/፡፡ በክርስቶስ ማመን መሳት ነው አሉዋቸው! የሕይወትን ውኃ ማግኘት መታለል ነው አሉዋቸው፡፡ ከሞት ወደ ሕይወት መሻገር ሞት ነው አልዋቸው፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን እንዲህ አሳምኖ እንዳይወስድባቸው በመጨነቅ ለመሆኑ ከተሳሳቱት ሕዝብ በቀር ከአለቆች ወይስ ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን?” ብለው ጠየቁዋቸው /ቁ.48/፡፡ አሁንም ብስጭታቸውን ቀጠሉና አስተምረውት የማያውቁትን ሕዝብ ሕግን ኦሪትን የማያውቀው ይህ ሕዝብ ርጉም ነው” ብለው ሕዝቡን መሳደብ ጀመሩ፤ ሎቱ ስብሐትና ክርስቶስን “ዕሩቅ ብእሲ” አድርገውት ፍጡርን የሚያመልኩ እነዚህ የተረገሙ ናቸው አሉ /ቁ.49/። የአምላካቸውን ድንቅ ሥራ አይተው ያመኑትን ሕዝብ ሕግን የማያውቁ እያሉ ወቀስዋቸው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሕዝቡ አምላኩን አውቆ ስላመነበት ሊበሳጩ አይገባም ነበር፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ሕግን የማያውቁና የተረገሙ ክርስቶስንም ከማመን የዘገዩ እነርሱ ራሳቸው ነበሩ /St. John Chrysostom, Homily 52/፡፡

 የሚደንቀው ግን ይህን አላዋቂነታቸው ይነግራቸው ዘንድ እግዚአብሔር በመካከላቸው ምስክር ማስቀመጡ ነው፡፡ እርሱም በሌሊት ቀድሞ ወደ ጌታ መጥቶ የነበረው የማታው ተማሪ ኒቆዲሞስ ነው /ዮሐ.3፡2/፡፡ ብስጭታቸውን በሰማ ጊዜ፣ ሕዝቡን አላዋቂ ሲሉት ባደመጠ ጊዜ፡-ኦሪታችን ሥራውን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ ሳይመረምር በሰው ላይ ይሙት በቃ ይፈርዳልን?” አላቸው /ቁ.50-51/ እውነት ነው! ኦሪት “ንጹሑን ሰው አትግደል” ትላለች /ዘዳ.19፡16-21/፡፡ ተራውን ሕዝብ በሕግ አፍራሽነትና በአላዋቂነት እየፈረጁና እየረገሙ እንጠብቀዋለን የሚሉትን ሕግ የሚያፈርሱት እነርሱ ራሳቸው ነበሩ፡፡ ስለዚህ አላዋቂዎች እነርሱ መሆናቸውን ኒቆዲሞስ ይነግራቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን አሁንም በኒቆዲሞስ ንግግር ተበሳጩ፡፡ “ለምን ታድያ ከገሊላ መጣ?” ብለው ከመጠየቅ ይልቅ ኒቆዲሞስን መስደብ ጀመሩ፡፡አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ነቢይ ከገሊላ እንዳይነሣ መርምር አንብብና እይ” ማለትን አስቀደሙ /ቁ.52/። ለምን ከገሊላ መጣ ብለው ቢጠይቁ ግን ክርስቶስ እርሱ ኢየሱስ ናዝራዊ ይባል ዘንድ በናዝሬት ገሊላ ያደገ ነገር ግን በቤተልሔም የተወለደ መሆኑን ባወቁ በተረዱ ነበር /ማቴ.2፡1 እና 23/፡፡ እነርሱ ግን ለስድብ ተቻኮሉ፡፡ በዚህ ንግግራቸው ኒቆዲሞስን እንደ አላዋቂ አድርገው በማየት መናቃቸው ነበር /St. John Chrysostom, Ibid/፡፡

 በመጨረሻም ምንም ሳይስማሙ  ተለያይተው እያንዳንዳቸው ወደየቤታቸው ሄዱ /ቁ.53/።

  ተወዳጆች ሆይ! ቅናት ክፉ ነው፡፡ ቅናት ዓይነ ልቡናን ያሳውራል፡፡ ቅናት ክርስቶስን ከማየት ይከለክላል፡፡ ቅናት ከዐለቱ (ከክርስቶስ) የሕይወት ውኃ እንዳንጠጣ ያደርጋል፡፡ ሀብታተ መንፈስ ቅዱስን እንዳንቀበል ያደርጋል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ጕድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፤ ድንጋይንም የሚያንከባልል ይገለበጥበታል” እንዳለ ቅናት የሚጐዳው ቅናተኛውን ነው /ምሳ.26፡27/፡፡ ቅናት ስለ እኛ የተቸነከረው በደምም የጨቀየውን ያ የፍቅር እጅ እንዳንመለከት ያደርጋል፡፡ ቅናት ተድላ መንግሥተ ሰማያትን እንድናጣ ያደርጋል፡፡ ወዮ አባት ሆይ! ራሳችንን እንዳንጐዳ በቅዱስ መንፈስህ ምራን! ከቅናት ከበቀል ጠብቀን! ፈሪሳዊ ቁጣና ብስጭት ከእኛ የራቀ ይሁን! አሜን! 

Thursday, August 9, 2012

ከሕዝቡ ግን ብዙዎች አመኑበት- የዮሐንስ ወንጌል የ34ኛ ሳምንት ጥናት


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

  ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ካላቸው እይታ አንጻር የሥነ መለኰት ምሁራን አይሁድን በሦስት ምድብ ይመብዋቸዋል፡፡ አንደኛው ምድብ የአለቆች፣ የካህናትና የፈሪሳውያን ምድብ ሲሆኑ እነርሱም ለክርስቶስ ፍጹም ጥላቻ የነበራቸው ናቸው፡፡ ሁለተኛው ምድብ ደግሞ በኢየሩሳሌም ውስጥ የሚኖሩና በአንደኛው ምድብ ባየናቸው ቡድኖች ጥላቻ ግራ የተጋቡ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች የአለቆቻቸውን ጥላቻ ቢያውቁም ጌታ በሚያደርጋቸው ገቢረ ተአምራት ፍጹም የሚማረኩ ናቸው፡፡ ጌታን ለአለቆቻቸው አሳልፈው እንዳይሰጡት በሚያስተምራቸው ትምህርት፣ በሚያሳያቸው ፍቅር፣ በሚያደርግላቸው ምልክት ልባቸው የተወሰዱ ናቸው፡፡ ሦስተኛው ምድብ ደግሞ ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ከኢየሩሳሌም ውጪ የሚኖሩ አይሁዳውያን ለገቢረ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጡ በክርስቶስ እጅግ የተማረኩና በምድብ አንድ ያየናቸውን አለቆች ስሜት የማያውቁ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች አለቆች ክርስቶስን ሊገድሉት እንደሚፈልጉ ሲሰሙ በእጅጉ የተደናገጡና በአለቆቹ ክፉ ሥራ ግርምት ውስጥ የገቡ ናቸው /Fr.Tadros Malaty,Commentary on the Gospel of John,pp359/፡፡

  አሁን ወንጌላዊው እየነገረን ያለው የሁለተኛው ምድብ የሆኑ ሰዎች ስሜት ነው፡፡ “እንግዲህ ከኢየሩሳሌም ሰዎች አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፡- ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህ አይደለምን? እነሆም፥ በግልጥ ይናገራል አንዳችም አይሉትም። አለቆቹ ይህ ሰው በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ በእውነት አወቁን? ነገር ግን ይህን ከወዴት እንደ ሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም” እንዲል /ቁ.25-27/። እንዲህ ማለታቸው ነበር፡-“አለቆቻችን እንገድለዋለን ብለው የሚዝቱበት ይህ አሁን በድብቅ ያይደለ በይፋ በስውር ያይደለ በግልጥ የሚያስተምራቸው አይደለምን? እነሆ፡- ከእናንተ ሕግን የሚያደርግ አንድ ስንኳ የለም ብሎ በግልጥ ይናገራል /ቁ.19/፤ ሆኖም ግን አንዳች ስንኳ አይሉትም፡፡ ወይስ ይህ ሰው በእውነት ክርስቶስ እንደሆነ አውቀዋል ማለት ነው? ይህ አሁን የሚናገረው ሰውዬ (ሎቱ ስብሐትና) ከቤተ ልሔም እንደተወለደ የቀራጩ የዮሴፍም ልጅ እንደሆነ እናውቃለን /ማቴ.2፡4/፡፡ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ኢሳይያስ፡- ትውልዱን ማን ይናገራል ብሎ እንደተናገረ ማንም አያውቅም” /ኢሳ.53፡8፣ Saint Cyril the Great/፡፡

 የእነዚህ ሰዎች ችግር ነቢዩ ኢሳይያስ የተናገረው ቃል ለቀዳማዊ ልደቱ ከማድረግ ይልቅ ለደኃራዊ ልደቱ አድርገው መረዳታቸው ነው፡፡ ነቢያቱ ግን እንዲህ የቀዳማዊ ልደቱ አይመረመሬነት እንደተናገሩ ሁሉ /ኢሳ.53፡8/ ሰው ሆኖ ከድንግል እንደሚወለድም በግልጽ ቦታውን ሳይቀር ጨምረው ተናግረዋል /ኢሳ.7፡14፣ ሚክ.5፡2/፡፡

   ከዚህ በኋላ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅደስ ሲያስተምር፡-እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔ ግን ከእርሱ ዘንድ ነኝ እርሱም ልኮኛልና አውቀዋለሁ” ብሎ ጮኸ /ቁ.28-29/። እንዲህ ማለቱ ነበር፡- “ጀሮ ያለው መስማትን ይስማ፤ ነቢያት አብዝተው እንደነገሯችሁ ከወዴት እንደሆንኩ (ናዝሬት ገሊላ እንዳደግኩ)፣ ከወዴት እንደተወለድኩ (ከቤተልሔም እንደተወለድኩ)፣ ከማን ወገን እንደተወለድኩ (ከዳዊት ወገን እንደተወለድኩ) ታውቃላችሁ፡፡ ሆኖም ግን ከአብ ባሕርይ ዘእምባሕርይ አካል ዘእምአካል የተወለድኩትን ቀዳማዊ ልደቴን ጨምረው የነገርዋችሁን አታውቁም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ይህን ከማመን ይህን ከመቀበል በፍቃዳችሁ ተከልክላችኋል ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ/St. John Chrysostom, Hom 50./፡፡ በእኔ ፈቃድ ብቻ ያይደለ በበአባቴም ፈቃድ ሰው ሆኛለሁና እርሱን ብታምኑበት እኔም ከእውነት የተወለድኩ እውነት እንደሆንኩ ባወቃችሁ ባመናችሁ ነበር፡፡ ደጋግሜ እንደነገርኳችሁ እኔ በህልውና ያየሁትን ነገርኳችሁ እንጂ አብን በባሕርይው ያየው አንድ ስንኳ የለም /ዮሐ.1፡18/፡፡ እኔ ልገልጽለት ያልፈቀደ፣ በእኔ ያላመነ ሁሉ አብን ሊያየው ሊያውቀው የሚችል እንደሌለ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ወልድን ያየ ግን አብን አይቷል ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እነግራችኋለሁ” /ዮሐ.14፡9፣ Augustine, On the Gospel of St. John, tractate 31/፡፡  

  ፈሪሳውያን ግን እንዲህ ስለተናገረ ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ከማር በሚጣፍጠው መለኰታዊ ቃሉ የሕዝቡን ልብ እንደወሰደ ወደ እውነትም እንደመለሰ ሲያውቁ ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፡፡ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ የሚሰቀልበት ሰዓት ስላልደረሰ በመለኰታዊ ሥልጣኑ ይህን እንዳያደርጉ ከለከላቸው፤ ስለዚህ ማንም እጁን አልጫነበትም /ቁ.30/።

  የፈሪሳውያን ቁጣ እየበዛ በሄደ ቁጥር ሕዝቡም እውነቱን እየተረዳ እያወቀ መጣ፡፡ ነገር ሁሉ ግልጽ እየሆነለት መጣ፡፡ ስለዚህ ከሕዝቡ ብዙዎች አመኑበት፡፡ ያመኑትም ሕዝብ እንዲህ ብለው ተነጋገሩ፡-አይሆንም አይደረግም እንጂ አለቆቻችን ይመጣል ብለው የሚነግሩን ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ይህ አሁን ያመንንበት ክርስቶስ ካደረጋቸው ምልክቶች በላይ ተአምራትን ያደርጋልን?” /ቁ.31/፡፡ የሚደንቅ ነው! ሕሙማነ ሥጋ በተአምራት ሕሙማነ ነፍስም በትምህርት ሲፈውሳቸው በዙርያ የነበሩ ድሆች አመንዝሮችና ቀራጮች አመኑበት፡፡ እናውቃለን ከሚሉት እረኞች ይልቅ የተበደሉት ሰዎች ዳኑበት፡፡ ቁስላቸውን ፈወሱበት፡፡ ስብራታቸውን ጠገኑበት፡፡ ተስፋቸውን ቀጠሉበት፡፡ ከውድቀታቸው ተነሡበት፡፡ አለቆች ነን ባዮቹ ግን አንዳችም ሳይጠቀሙ ከነደዌአቸው ቀሩ፤ ወደ ሐኪማቸው ከመቅረብ ተከለከሉ፤ ይባስ ብለውም ሊገድሉት ፈለጉ፡፡
  ሕዝቡ ሰለ ክርስቶስ እንደዚህ ሲነጋገሩ ሲሰሙም ሎሌዎቻቸውን ላኩ /ቁ.32/። ሰው ወዳጁ ጌታ … ሰው አፍቃሪው ንጉሥ ግን እንዲህ አላቸው፡-“ፈሪሳውያን ሆይ! በዚህ ዓለም ከእናንተ ጋር ብዙ እንደምቆይ ስለምን ትቆጣላችሁ? ሸክም እንደሆንኩባችሁ አውቃለሁ፡፡ ክፋታችሁን በእውነት ስለምናገርባችሁ አውቃለሁ፡፡ ሰላም እንደነሣኋችሁ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን እኔ ሳልፈቅድላችሁ ማድረግ አትችሉምና ጊዜዬ ሳይደርስ እኔን ለመግደል በከንቱ የምትደክሙ አትሁኑ፡፡ በቅናትና በቁጣ ተነሳሥታችሁ እኔን ለመግደል የምትቻኮሉ አትሁኑ፡፡ ድኅነተ ዓለም የምፈጽምባትን የእኔን ሰዓት፣ በእኔ ዘላለማዊ ዕቅድ ውስጥ ያለችውና መከራ መስቀልን የምቀበልባት ያቺ ሰዓት ስትደርስ በፈቃዴ፣ ወድጄ ራሴን እሰጣችኋለሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ በኋላ ግን ሥራችሁ ክፉ ነውና ፈጽሞ አታገኙኝም፤ በጨለማ መኖርን የምትወዱ ናችሁና ወደ ብርሃን መውጣት የማትፈልጉ ናችሁና ስለዚሁ በእናንተ ዘንድ የማድር የምዋሐድ አይደለሁምና አታገኙኝም፡፡ አንድም ጥጦስ መከራ ሲያደርስባችሁ ትሹኛችሁ፤ አታገኙኝም፡፡ አንድም ጻድቃንን ልፈርድላቸው ኃጥአንን ልፈርድባቸው በመጣሁ ጊዜ አምነንበት ቢሆን ብላችሁ ትፈልግኛላቹ፤ አታገኙኝም፡፡ መንገዱም እውነቱም እኔ ነኝና በእኔ ሳታምኑ ተድላ ደስታ ወዳለባት መንግሥተ ሰማያት መምጣት አይቻላችሁምና አታገኙኝም፡፡ ፈሪሳውያን ሆይ! ጥቅም በሌለው ምክር ራሳችሁን የምታጎሳቁሉ አትሁኑ፡፡ አለቆች ሆይ! መከራ ነፍስ የሚያመጣባችሁ ነውና ቁጣችሁን ወደ ሰገባው መልሱት፡፡ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና እነሆ የተወደደ ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ የመዳን ቀን አሁን ነው /2ቆሮ.6:2/፡፡ አትሳቱ! ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና የዘለዓለምን ሕይወት ታጭዱ ዘንድ በመንፈስ የምትዘሩ ሁኑ /ገላ.6፡7-8/፤ በእኔ እመኑ በአባቴም እመኑ፡፡ እኔስ ሞታችሁን እገድል ዘንድ እናውቀዋለን ከምትሉት ሆኖም ግን ከማታውቁት ከአባቴ ዘንድ መጥቻለሁና፣ ሕይወት ይሆንላቸው ዘንድ ለወደዱ ሕይወትን እሰጣቸው ዘንድ ሰው ሆኛለሁና ሞት በእኔ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡ ሰዓቱ ሲደርስ ግን የሲዖል የምሥጢር በሮችን እሰባብራለሁ፡፡ ምርኮን እማርካለሁ፡፡ ስለዚህ እናንተ እንደምታስቡት ፈጥነንም እናስወግደው እንደምትሉት በመቃብር በስብሼ የምቀር አይደለሁም፡፡ ከሙታን ተለይቼ እነሣለሁ እንጂ፡፡ መነሣትም ብቻ ሳይሆን ደቀመዛሙርቴ እያዩኝ በይባቤ መላዕክት በቅዳሴ በብርሃን በሥልጣን ዐርጋለሁ /መዝ.46፡5/፡፡ ያኔ ሰዎች ዕርገቴን አይተው ያደንቃሉ፤ መላእክትም፡-“ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድነው?” ይሉኛል፤ እኔም “በወዳጆቼ ቤት የቆሰልኩት ቁስል ነው” እላቸዋለሁ /ቁ.33-34፣ ዘካ.13፡6፣ St. Augustine: On the Gospel of St. John, tractate 31:9/፡፡

  ከዚህ በኋላ አይሁድ፡-እኛ እንዳናገኘው ይህ ወዴት ይሄድ ዘንድ አለው? በግሪክ ሰዎች መካከል ተበትነው ወደሚኖሩት ሊሄድና የግሪክን ሰዎች ሊያስተምር አለውን? እርሱ። ትፈልጉኛላችሁ አታገኙኝምም እኔም ወዳለሁበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም የሚለው ይህ ቃል ምንድር ነው?” ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ /ቁ.35-36/።

  ቸርነትህ የበዛ አፍቃሪያችን ሆይ! በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበን፡፡ ቀን ሳለልን በብርሃን እንድንመላለስ እርዳን፡፡ ዓለምን ለማሳለፍ በመጣህ ጊዜ ያ የቀመስነውና የለመድነው የፍቅር ፊትህ በምግባራችን ክፋት እንዳይለወጥብን ዛሬ ላይ በምግባር በትሩፋት እንድንመላለስ እርዳን፡፡ ሙሽራችን ሆይ! ዘይታችን አልቆ ከውጭ ከሚቀሩ ቆነጃጅት እንዳንሆን ደግፈን፡፡ የአባቴ ብሩካን ከምትላቸው ወዳጆችህ ጋር ደምረን፡፡ አሜን በእውነት አሜን!!!!!!!

FeedBurner FeedCount