Friday, March 21, 2014

መጻጉዕ ዘቀዳሚት ሰንበት



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 12 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

 በስሙ ስሙን አግኝታችሁ፣ በእርሱ የምትገቡ፣ ምርጦች ሆናችሁ የተጠራችሁ፣ የጨለማ ስራን አስወግዶ ወደሚደነቅ ብርሃን ያወጣችሁ፡፡ በይቅርታና በፍቅር ወደ እናንተ የመጣ ክርስቶስን ከላይ እንደ ልብስ ከውስጥ ደግሞ እንደ አካል የለበሳችሁት፣ ኃጢአትና ልምምዷን አሸንፎ በአባታዊ ፍቅር ልጅነትን ያደላችሁ ሁላችሁ በእርሱ በእግዚአብሔር ልጅ ሰላምታ ሰላም ይሁንላችሁ::


  ዛሬም ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሰው ከምሥጋና አላረፈም:: ለእኛ አልገለጥ ያለን እንደ መብረቅ ብልጭታ እንኳን ያላየነውን የመላእክት የምሥጋና ሕይወት አይቷልና ምግቡን ከመላእክቱ ጋር ቀላቅሏል:: ዛሬ ቀዳሚት ሰንበት ነው:: ለሰው ልጆች ዕረፍተ ሥጋ የተሠራበት ቀን ነው:: 22 ፍጥረት ሲፈጠር 23ኛው ግን 22 ፍጥረታት ዕረፍት ተፈጠረች:: ይህንን ቀን ጌታ ቀኑን ብቻ ፈጠረው፤ ሰንበት የዕረፍት ቀን አደረገው:: ታዲያ እንደ ሌሎች ሳምንታት ቅዱስ ያሬድ የዚህ ቀን ድርሰቱ በጣም አጭር ነች:: ግን ምሥጋናው አዲስ ነውና ጥቂት ቃላትን እነሆ!!!

  መስቀል አብርሃ አብርሃ ወተሠብሐመስቀል እጅጉን አበራ፤ በዚህ እንጨት መስቀል ሁላችን ያመንን ከጠላት ዳንን::” ለእኛ የመስቀሉ ነገር የዓለም ሳይሆን ሰማያዊ ጥበባችን ነው:: በሞኝነት እንዲኖሩ የመስቀሉ ነገር ካልተረዳቸው እራሳችንን አንቆጥርም::

  መስቀሉሰ ለክርስቶስ ብርሃን ለእለ ነአምን ትብል ቤተክርስቲያንቤተክርስቲያን የክርስቶስ መስቀል ለምናምንበት ብርሃን ነው ትላለች::” ለመርከቦች ወደብ፣ ለባሕር ጸጥታ፣ በምድረበዳ ለሚቸገሩ እርሱ በጸጋ ያድናል፤ እርሱም መስቀል ነው:: በችግር ላሉ፣ በእስር ላሉ፣ በምድረበዳ ላሉ፣ ዛሬ ለሚቸገሩት፣ ሕይወት የማይወጣ ዳገት ለሆነባቸው ሁሉ መስቀሉ መድኃኒት ነው::

 ሶበሰ ይሠርቅ ፀሐይ ንህነኒ ንርከብ ሰላመፀሐይ በሚወጣበት ጊዜ ሰላምን እናግኝ:: በመስቀል በመታመን አምነንአሜን” ብለን ልባችንን አጽንተን ጽዮንን እንሳለማት::” በሕይወታችን መልካሙ ሁሉ በሆነ ጊዜ ወይም በልጅነታችን በክርስቶስ አምነን ለነገ የሚሆን ሥንቅን እናከማች:: አሜን!

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount