Friday, March 7, 2014

ቅድስት ዘቀዳሚት ሰንበት


በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ የካቲት 28 ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ

ጸልዩ እምቅድመ ንባበ ዝንቱ ክርታስ

 በብሉይ ለሰራት በሐዲስም ለሰው ልጆች ማደሪያውን ያዘጋጅ ዘንድ በመቃብር ባደረባት በቀደመችው ሰንበት ቅዱሱ የእግዚአብሔር ሰው ያሬድ የዚህ ሳምንት ድርሰቱን በፈጸመባት በዚህች ዕለት እርሱ ለቤተክርስቲያን በሚሰጠው ሰላምበሀክሙሰላማውያን ሰላም ያደራችሁ ሰላም ያድርጋችሁ ብዬ ሰላምታዬን ወደ እናንተ ላክሁ፡፡


 ዛሬ አባታችን የድርሰቱ መጀመሪያም መጨረሻም ያደረገው የዕፀ መስቀሉን ነገር ነው፡፡ ድርሰቱም ከሌሎች ቀናት በጣም ያጠረች ናት፡፡ ሆኖም ዛሬም እንደወትሮው ከማያልቀው ምስጋና እነሆ ጥቂት ቃላትን እንመልከት፡፡

 በአፍአኒ መስቀል በውሣጢአኒ መስቀል . . . ጽልመትን ሲያበራ በውስጥ መስቀል በውጪም መስቀል በምድረ በዳም መስቀል፡፡የመስቀሉ ነገር በአንገታችን በውጪ አንጠልጥለን በውስጥ ደግሞ ለገላትያ ሰዎች በሆነ ልብ ሳይሆን ለአምላክ በሆነ ልብ ስለን እንኖራለን፡፡ ስንቀመጥ፣ ስንነሳ፣ ስንጓዝ በሁሉም ቦታ መስቀል መለያችን ነው፡፡ ስንበላ ስንጠጣ፣ ስንጀምር ስንፈጽም በመስቀል እናማትባለን፡፡ ስለዚህ በውስጥም በውጪም መስቀሉ ተስሎብናል፡፡
  መስቀል ብነ ንሕነ . . . መስቀላችን እኛ ስንማጸን አድነን፡፡እኛን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ በዚህ መስቀል የሰጠን ተስፋ ድንቅ ነው፡፡

 በኢየሩሳሌም ሰቀልዎ በጎልጎታ ቀበርዎ . . . በኢየሩሳሌም ሰቀሉት፤ በጎልጎታ ቀበሩት፤ ከመስቀሉ ወርዶ ለሁሉ ሰላምን አደረገ፡፡በሞቱ ሕይወትን ሰጠን፡፡ ያውም በእኛ ርግማን ገብቶ የመስቀልን ሳይሆን የሰውን ርግማን አጠፋ፡፡ እንደ ኖህ ርግብ የሰላምን ነገር በእንጨቱ አበሰረን፡፡ ሰላምንም በምድር በሰማይ ሠራ፡፡

 ጹሙ ወጸልዩ በንጹሕ ልብ - ጹሙ፤ ጸልዩም፡፡ የመስቀሉን ኃይል ተመርኮዙ፤ ቤተክርስቲያንንም አጥብቃችሁ ያዙብሎ ከነገረን በኋላ መክሮን ይለየናል፡፡

 በሀ በልዋ ተሳለምዋ ጊሡ ሃቤሃ. . . ሰላም በሏት፤ ሰላምታንም አቅርቡላት፡፡ ወደ እርሷ ገስግሱ፤ ከእርሳም አትራቁ፡፡ ሰላማዊ ጽዮን ለሁሉ ታበራለችበማለት የዕለቱን ድርሰቱን ፈጸመ፡፡ እኛም አዲሱን የጾም ሳምንት ነገ እስክንይዝ ድረስ ሰላም ያቆየን፡፡
 ለእርሱ ልጅነት የማልበቃ ደካማ ስሆን የማይገባኝን ነገር ስለፃፍኩ ስለእኔ ፀልዩልኝ፡፡ አሜን በጾሙ ሰላምን ይስጠን ጾሙን በሰላም ያስፈጽመን አምላከ ቅዱስ ያሬድ ይጠብቀን፡፡

No comments:

Post a Comment

FeedBurner FeedCount