Saturday, May 5, 2012

በአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል ላይ የሚነሱ አንዳንድ ጥያቄዎች- (ለፕሮቴስታንቶችና ተሐድሶዎች የቀረበ)- ክፍል አንድ!=+=

አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሰማዕትነት ሞተው ቅዱስ ጳውሎስ “እርሱንና የትንሣኤውን ኃይል እንዳውቅ በመከራውም እንድካፈል ወደ ሙታንም ትንሣኤ ልደርስ ቢሆንልኝ በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ” ያለውን ለመፈጸም ይመኙ ነበር /ፊሊ.3፡11/፡፡ ነገር ግን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደዌ ዘእሴት (ዋጋን በሚያሰጥ የሆድ ሕመም) እንዲሞቱ ነው የፈቀደላቸው፡፡ በዚህ አሟሟታቸውም ከጌታችን መከራ መስቀል እንደሚያሳትፋቸው እንደ ሰማዕትነትም እንደሚቆጠርላቸው ነው የተነገራቸው፡፡ ይህ ደግሞ ፍጹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት እንጂ መጽሐፍ ቅዱስን የሚቃረን አይደለም፡፡ ኢዮብን ስንመለከተው በደዌ ተልቶ ሸቶ ነበር፡፡ እንዲህ መሆኑ ግን ለጥቅሙ ነበር፡፡ ጳውሎስን ስናይ የጐድን ውጋት ነበረው /2ቆሮ.12፡7-10/፡፡ ነገር ግን ለጥቅሙ የተሰጠው ነበረ፡፡ ጢሞቲዎስን ስንመለከት የሆድ ሕመም ነበረው /1ጢሞ.3፡25/፡፡ ነገር ግን ለጥቅሙ ነበረ፡፡ ታድያ አቡነ ተክለሃይማኖት ዐስበ ሰማዕትነት (የሰማዕታትን ዋጋ) የሚያገኙበት ሕመም ያዛቸው ቢባል ምንድነው ብርቁ? አቡነ ተክለ ሃይማኖትም በዐረፍተ ዘመናቸው መጨረሻ የያዛቸው ደዌ ዘዕሴት ነበረ ቢባል ምንድነው ድንቁ? የክርስቶስን መከራ የሚያሳትፍ እንጂ የክርስቶስን መከራ የሚተካ አልተባለም፡፡ እንግዲያውስ ወንድሞችና እኅቶች! ያልተባለውን ተባለ፣ ያልተፈጠረውን ተፈጠረ፣ ያልተጣፈውን ተጣፈ እያልን ውሸት ከመናገር ብንቆጠብስ?(ይቀጥላል!)

 ተመሳሳይ ገጾች

 አባታችን ተክለሃይማኖት ማለት እኒህ ናቸው

2 comments:

  1. በመጀመሪያ ፕሮቴስታንትና ተሐድሶዎች ላሉት፦ ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም! ሰውን ግራ ለማጋባት የተጠቀሙበት ነው። ተሐድሶ የቤተክርስቲያን ቋንቋ ነው። መልካም ቋንቋ ነው። ለመናፍቃን ሊሰጥ አይገባውም። የክርስቲያኖችን ሕይወት ለማደስ፣ የተበላሸ ነገርን ሁሉ ለማደስና በጎ ለማድረግ የምንጠቀምበት ቃል ነው። ተሐድሶ ብለው ራሳቸውን የሚጠሩ መናፍቃን ናቸው፡፡ ሁለተኛ፦ መናፍቅ ሁሉ ይህን አለ ያን አለ ብለን መልስ መስጠት ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም ለማወቅ ሳይሆን በትእቢት ለስድብ ስለሚናገሩ የተቀደሰውን ለውሶች መስጠት እንዳይሆን።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ዛሬስ ተሀድሶ የለም የሚለውን ቃል ደፍረሽ ትናገሪ ይሁን? ማንም ይበል ኘሮቴስታንትም ሆነ ሙስሊምም ይበል ነገር ግን የሰው ልጅ ጥያቄ ከሆነ መልስ መሰጠት አለበት፡፡ አንድ ሰውም ቢሆን በቤተክርስቲያን የአስተምሮና ባለው አምልኮት ጥያቄ መፈጠር የለበትም መመለስ አለበት፡፡ የአንድ ሰውም ውድቀት ቢሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ፈቃዱ አይደለም፡፡ እህቴ እንዴት እንደተረዳሽው አላውቅም፡፡ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሳምራዊቷን ሴት ለአንዲቷ ሴት ነው ያንን የመሰለ ወንጌል ያስተማራት፡፡ የሐ 4፣ ማስተዋሉን ይስጥሽ፡፡

      Delete

FeedBurner FeedCount